ኤርዶጋን አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ በሶሪያ እና በቱርክ አዋሳኝ ድንበር ላይ እንዲዘጋጅ አሳስበዋልየቱርክ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እንዳስታወቁት ከሆነ አንካራ በሶሪ…

ኤርዶጋን አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ በሶሪያ እና በቱርክ አዋሳኝ ድንበር ላይ እንዲዘጋጅ አሳስበዋል

የቱርክ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እንዳስታወቁት ከሆነ አንካራ በሶሪያ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ ና በቱርክ ቁጥጥር ስር ያሉ ሁለት አካባቢዎችን ለማስተሳሰር መታሰቡ በቱርክ-ሶሪያ ድንበር ላይ ዳግም ጦርነት እንዳይፈጠር ስጋት መፍጠሩንም ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ሰኞ የተካሄደውን የካቢኔ ስብሰባ ተከትሎም ኤርዶጋን እንደተናገሩት ዘመቻው ቱርክ ከሶሪያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ 30 ኪ.ሜ ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማስቀጠል ያለመ ነው ብለዋል።

“በደቡብ ድንበራችን ላይ ባቋቋምነው 30 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ያለው አስተማማኝ ቀጠና ላይ የጀመርነውን እቅድ በተመለከተ በቅርቡ አዳዲስ እርምጃዎችን እንወስዳለን” ብለዋል ኤርዶጋን።

ፕሬዝዳንቱ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ከመስጠት ቢታቀቡም ዘመቻው ወደ ተግባር መግባት የሚጀምረው የቱርክ ወታደራዊ ሃይል ፣ የመረጃ እና የደህንነት ሃይሎች ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ መሆኑንን ጠቁመዋል።

የታቀደው ወታደራዊ ዘመቻ ኢላማ የተደረገበት ቦታ በሶሪያ ሃይሎች እና የኩርድ ታጣቂ ቡድን መሰባሰቢያም መሆኑን የአልጀዚራ ዘገባ አትቷል፡፡

ረድኤት ገበየሁ

ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply