ኤርዶጋን የሶስት ወራት ጊዜያዊ አዋጅ አወጁ፡፡የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶጋን የመሬት መንቀጥቀጡ በደረሰባቸው አካባቢዎች ሶስት ወራት የሚቆይ አዋጅ ማወጃቸው ታውቋል፡፡ፕሬዝዳንቱ ለተ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/bf7eUO2uJxdTQEBq0i1FRXVEetPkL2UhjXq8vNoQWxcI5AxJ9-M_ksxRRVpxDXPs7jnUh8vUJf595qIIo39ysE5pRMrWLy42D3U1_FYNyQv7awIWPVuzUM6Pxz92ACghw0ujHVgJYrNYy5XyELSVNxypuWNddag9vR8WMHLnKKpPhzNqCBQ6VRnq4eoRZ63JuHg2NW6iLM5KsYVh3bnIlUfYp6TzmGz8WDX1kotrPGHGh21YtPOgI8j1_dGQy0ctMO6y5HQMEk4WaCsa4jLXZoFWSSV_2mvNi2hEkevzdU_9V-tSlzx17l6wbHCdH9oztdhTYBYxjIdH7_2V1cWLYg.jpg

ኤርዶጋን የሶስት ወራት ጊዜያዊ አዋጅ አወጁ፡፡

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶጋን የመሬት መንቀጥቀጡ በደረሰባቸው አካባቢዎች ሶስት ወራት የሚቆይ አዋጅ ማወጃቸው ታውቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለተጎጂዎች አስፈላጊውን ሁሉ እየተደረገላቸው ይገኛል ያሉ ሲሆን ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

አሁንም የህይወት አድን ስራው በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛልም ተብሏል፡፡

ሰኞ ረፋድ በቱርክ እና በሶሪያ ድንበር ላይ በደረሰው ርዕደ መሬት ከ4 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የነፍስ አድን ሠራተኞች በርካታ ተጎጂዎችን እያገኙ መሆናቸውን ከግምት በማስገባት፣ የጉዳቱ መጠን ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚገኙ በርካታ ሰዎች ወደ መኖሪያ ህንፃዎቻቸው ለመመለስ ስጋት እንዳለባቸውም ተነግሯል፡፡

ከርዕደ መሬቱ በኋላም በነበረው የመሬት መንቀጠቀጥ ሳይበገሩ አንዳንድ የነፍስ አድን ሠራተኞች በህይወት የተረፉ ሰዎችን ህይወት ለማዳን በባዶ እጃቸው ጭምር ፍርስራሾችን እየቆፈሩ ፍለጋቸውን ቀጥለዋል።

ርዕደ መሬቱ በቱርክ በሚገኙ ሦስት አየር ማረፊያዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ለዕርዳታ አቅርቦት ፈተና መፍጠሩን ሮይተርስ ዘግቧል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቱርክ ሊግ ሊደረጉ የነበሩ ሁሉም ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ መራዘማቸው ታውቋል፡፡

በቱርክ ድንበር ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች በሚኖሩባት ሶሪያም ቢያንስ 1,400 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply