ኤች አይ ቪ ኤድስ አሁንም ትኩረት የሚያሻው የማህበረሰብ ስጋት ነው—ጤና ሚንስቴርበኢትዮጵያ የወጣቶች በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ እንደ አዲስ የመያዝ ምጣኔ አሁንም ከፍተኛ ስጋት ሆኖ መቀጠሉንበ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/YueMPrbBvFrmU5Xc2l8GweYB6knQm1Dw1Kd846fYLqIys6dGLLSoYrm0LjKk0CaNqpWqRRlL35wxexUIJM14Z6B_9-iwyfAsJX56-Z3PRBUDvvJtvg05aIrmXyzKG4mP2NklTAlb5m9J-xDfH7wYCViOKNabfFE4N6CgCbjxL3McHPgcNbtj7wdhk7AwStsDx6FW1cHr4iyKtZHAklgELb940_xj20R7J7vGgSdoURj3dL9bTnKRekazPBJdfMiWdP9DcuFzt0IoyOxJ4tFbuTdrpGXDOsC7-5eh_a39JkTI6V5ZdoOPs5ok43sUf61UQXQLwS8VvT8NxLVvVi7y4w.jpg

ኤች አይ ቪ ኤድስ አሁንም ትኩረት የሚያሻው የማህበረሰብ ስጋት ነው—ጤና ሚንስቴር

በኢትዮጵያ የወጣቶች በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ እንደ አዲስ የመያዝ ምጣኔ አሁንም ከፍተኛ ስጋት ሆኖ መቀጠሉን
በጤና ሚኒስቴር የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ፍቃዱ ያደታ ተናግረዋል፡፡

ዶክተር ፍቃዱ እንደገለጹት፤ ወጣቶች የኤች.አይ.ቪ ቫይረስን በተመለከተ ግንዛቤው ቢኖራቸውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በወጣቶች ላይ የመዘናጋት ድርጊቶች እየተበራከቱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ይህም የሚያሳየው ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በሀገሪቷ ያለው የወጣቶች በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ እንደ አዲስ የመያዝ ምጣኔ አለመቀነስ ሊያሳስበው እና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም እየተስተዋሉ ያሉ መዘናጋቶችን ለመቅረፍ ለወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ዳግም ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ግን ቫይረሱ እንደ ወረርሽኝ የማይከሰትበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ታህሳስ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ
መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8)

Source: Link to the Post

Leave a Reply