ኤፍ ኤንደ ቲ (F & T) ኬብል ማኑፋክቸሪንግ  የተባለ የቻይና ካኩባንያ  በሃገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ገመዶችን ማምረት መጀመሩን አስታወቀ። የድርጅቱ ባለቤት  ሚር ፎ እና ሚር ፍራንክ  እደ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/qaI9SReJV1rzPig4qnnLpys4d_TJBzThO6k65B4IgJ3Y60Mo7wt_LTE9rxAjr1wU9RrtOgwtDOYY0ZO528olUnUKESje0SADaU9MJlLcHKX3htX9vl7F4wKVfwA-NgaM51ylXkVJQrVFNJ57ZfHmEaUsV3EEBH1rPiA3L1_SAr9jrKQZyJEpgjsRweVJDzjC-0ZOwu6PSP3GdM7qHGEC8LQLaMIq8mybeAtNBGY7YVHYnRc4pM2dtv_TIG9CRqL2kvBufVKbkiJvEjEVrYy_d1NGtvHueihk4_VNr8GlbPb7bL4kVEUZMYWQ1UQ31X_eQLnb6oW-lR2StlZqTnXkBw.jpg

ኤፍ ኤንደ ቲ (F & T) ኬብል ማኑፋክቸሪንግ  የተባለ የቻይና ካኩባንያ  በሃገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ገመዶችን ማምረት መጀመሩን አስታወቀ።

የድርጅቱ ባለቤት  ሚር ፎ እና ሚር ፍራንክ  እደገለፁት ይህ አምራች ካምፓኒ የሚገኘዉ  በሰበታ በተለምዶ ዲማ እየተባለ በሚጠራዉ  አከባቢ ነዉ ።

ወደሃገር ዉስጥ ከገባ አንድ አመት የሞላዉ ሲሆን፤ የጥራት ማረጋገጫ ወስዶ የኤሌክትሪክ ፓዎር  ገመድ ወይንም ኬብል በአሁን ሰዓት  በማምረት ላይ ይገኛል ብለዉናል ፡፡

ኤፍ ኤንደ ቲ የተሰኘዉ ድርጅት በ5 ሚሊዮን ዶላር  ወደ ገበያዉ መግባቱንም ባዘጋጁት ሴሚናር ላይ  ነግረዉናል ፡፡

ድርጀቱ  ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ እንደ ገለፀው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ ያለ በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ጥራቱ የተረጋገጠ የኤለክትሪክ ኬብሎች ያስፈልጋል ብለዋል።

በመሆኑ በዚህ ዘርፍ ላይ በትኛዉም ሃገርና ቦታ ላይ የሚሰሙና የሚታዩ የኤሌክትሪክ ኬብል ጥራት ችግር ለመፍታት አቅደን ነዉ ወደ ገበያዉ ለመቀላቀል የወሰነዉ ብለዋል ፡፡

ከኤሌክትሪክ ኬብል በተጨማሪ ከኤሌክትሪክ ጋር የሚገናኙ ሌሎች ምርቶችን እያመረተ ለገበያው የማቅረብ ፍላጎት አለው ነው የተባለው።

በተጨማሪም ይህ ካንፓኒ በገበያዉ እንዳለዉ የኮፐር መጠን በወር 3 መቶ ቶን ያህል  ኮፐር የማምረት አቅም አለዉ ብለዉናል ።

በመጨረሻም ይህ ኤፍ ኤንደ ቲ ኬብል ማኑፋክቸሪንግ በቻይና ውስጥ የታወቀ እና ባለቤቶቹ ከዚህ ቀደም በቻይና ዉስጥ ለ 15 ዓመት በዘርፉ ላይ መስራታቸዉን ሰምተናል፡፡

ልዑል ወልዴ

Source: Link to the Post

Leave a Reply