
በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ለወራት የዘለቀው በፋኖ ታጣቂዎች እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል የሚካሄደው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ቢቢሲ ከተለያዩ ስፍራዎች የሚያገኛቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። ትናንት እሁድ መስከረም 14/2016 ዓ.ም. በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መዋሉን መዋሏን ነዋሪዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተለይ በከተማዋ ውስጥ በሚገኙት ማራኪ፣ ልደታ እና ቀበሌ 18 ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ከፍተኛ ተኩስ እንደነበር ተናግረዋል።
Source: Link to the Post