“እህል ከቀመስን ሳምንት ቆጥረናል፤ አፈር እየበጠበጥን ነው ለልጆች የሰጠናቸው!” በወለጋ ጫካ ለ8 ቀናት ተጉዘው ራሳቸውንናቤተሰባቸውን ከኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ የጭካኔ ጥቃት የታደጉ የጊ…

“እህል ከቀመስን ሳምንት ቆጥረናል፤ አፈር እየበጠበጥን ነው ለልጆች የሰጠናቸው!” በወለጋ ጫካ ለ8 ቀናት ተጉዘው ራሳቸውንናቤተሰባቸውን ከኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ የጭካኔ ጥቃት የታደጉ የጊ…

“እህል ከቀመስን ሳምንት ቆጥረናል፤ አፈር እየበጠበጥን ነው ለልጆች የሰጠናቸው!” በወለጋ ጫካ ለ8 ቀናት ተጉዘው ራሳቸውንናቤተሰባቸውን ከኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ የጭካኔ ጥቃት የታደጉ የጊዳ ወረዳ ነዋሪ ከተናገሩት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓም አዲስ አበባ ሸዋ ከኦነግ ሸኔ እና ከጥፋት ተባባሪዎቹ ከህዳር 29 ቀን ጀምረው በጊዳ ወረዳ ድሬ ቀበሌ ከፈፀሙት አሰቃቂ ጥቃት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ለመታደግ ሲሉ የመንፈቅ እና የ2 ወር ህጻናትን ሽኮኮ በማድረግ ሌሎች አቅመ ደካሞችን እናቶችንና አባቶችን በመያዝ ለ8 ቀናት በጫካ ቆይተዋል። “እህል ከቀመስን ሳምንት ቆጥረናል፤ አፈር እየበጠበጥን ነው ለልጆች የሰጠናቸው!” ሲሉ የነበረውን አሳዛኝ ቆይታ አስተውሰዋል። ከ8 ቀናት ረሃብና ውሃ ጥም የበዛበት ስቃይ ቆይታ በኋላ መከላከያ ወዳለበት አካባቢ ደርሰዋል። በሽብር ተግባር የተሰማሩት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለቀናት በአማራ ተወላጆች ላይ አሰቃቂ ግድያ መፈፀማቸውና በሽህዎች የሚቆጠሩትን ማፈናቀላቸውን ያወሱት ምንጫችን የድሬ ቀበሌም ሆነ የጊዳ ወረዳ የመስተዳድር አካላት ኦነግ ሸኔዎች የት እንዳሉ ያውቃሉ፤ ገበያ ላይ ህዝቡን ሰብስበው በአማራ ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ በዛቱ በሳምንቱ ነው ጥቃቱን እንደፈፀሙት እናውቃለን ብለዋል። 16 የሚሆኑ ከብቶቻቸውን ከቀናት በፊት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቻቸው እንደዘረፏቸውም ተናግረዋል። ከሳምንት የበርሃ ጉዞ በኋላ ቀድመን ያገኟቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላትም እየተራቡና እየተጠሙ ያሉ ህጻናትን፣አቅመ ደካሞችንና ሴቶችን ወደ ከተማ ለመላክ በሚል የወረዳ አስተዳዳሪው ሾፌርና ተሽከርካሪ እንዲመድቡ ቢጠይቋቸውም መኪና የለንም፤ በእግራችሁ መጓዙ ትችላላችሁ በማለት ጭካኔያቸውን አሳይተዋል። በመከላከያ ሰራዊት ተገደው ተፈናቃዮችን በባለሀብት ኤፍ ኤስ አር ወደ ጊዳ ከተማ እንዲገቡ ከተደረገ በኋላም 103 ሆነው “ልብስ የለንም ምን እንልበስ? ተባበሩን” ብለው ጠይቀዋል፤ “እናንተ በመከላከያ ሀይል የምትታጀቡ ሰዎች ናችሁ” በሚል የፀጥታ ሀይል በመጥራት ከቢሮአቸው ስላስወጧቸው ዘመድ አፈላልገው ለመጠጋት ተገደዋል። አሁን ላይ “ህግ አለ?ወይም መንግስት አለ ወይ?” ብለን ለመጠየቅ ተገደናል ብለዋል የጊዳ ወረዳ ነዋሪው ። የፌደራል እና የአማራ ክልል መንግስት በአስቸኳይ እጁን አስገብቶ ከቀበሌ እስከ ክልሉ ድረስ የነገሰውን ኢፍትሃዊነት በመገምገም እንዲያስተካክሉ ተጠይቋል። በመጨረሻም የሚመለከተው የበላይ አካል ገብቶ መዋቅሩን ይፈትሸው፤ እኛን አማራዎችንም መንግስት እንደ ዜጋ ቆጥሮን ከጨካኞች ግድያ የመታደግ ኃላፊነቱን ይወጣ ሲሉ ጥሪ አድርገዋል። ሙሉ ቃለ ምልልሱን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply