
“እራሳችሁን ለማታለል አትሞክሩ!” ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ይህ ፎቶ የራሱ የታላቁ እስክንድ ነጋ ነው። የከተማውመናኝ፣የማይሰበረው፣የፅናት ተምሳሌቱ፣ብረቱ፣ሐቀኛው፣የዘመኑ ክስተት… ወዘተ የመሳሰሉት መጠሪያዎች የተሰጡት እንዲህ በዚህ ዘመን ይደረጋል ተብሎ የማይታሰበውን ማድረግ ስለሚችል ነው። ለታለቁ እስክንድር ነጋ ስልጣን፣ዝና፣ጥቅም፣ገንዘብ፣ጨርቅ ባጠቃላይ ብልጭልጭ ዓለማዊ እና ስጋዊ ነገሮች ምንም ናቸው። እርሱ ከዚህ ተሻግሮ እራሱን ጎድቶ ለሰው የሚኖር ነው። ይልቁንስ በትግል እና በምስኪኑ ስም እየነገዳችሁ ለስልጣን፣ለዝና፣ለከርሳችሁ እና ለገንዘብ ስትሉ ለዚህ እርግማን ሥርዓት እና ለዕርኩስ መንፈስ አሽከር የሆናችሁ ለራሳችሁ እዘኑ። ለራሳችሁ አልቅሱ። እራሳችሁን እየዋሻችሁ ከዕውነት ተጣልታችሁ፣ በህሊና ጎድፋችሁ፣በመንፈስ ቆሽሻችሁ ኑሩ።
Source: Link to the Post