እርዳታ የሚሹ ዜጎች ቁጥር  እና  በማህበሩ ያለው የግብአት ክምችት አልተመጣጠነም ተባለ

በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ ጉዳት እርዳታ የሚሹ ዜጎች ቁጥር እና በማህበሩ ያለው የግብአት ክምችት ሊመጣጠን ባለመቻሉ ተቸግሪያለው ሲል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታውቋል፡፡

ማህበሩ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች እርዳታ የሚያደርግ ሲሆን፤ በዘንድሮ ዓመት በበርካታ አከባቢዎች በተከሰቱ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ጉዳቶች እርዳታ የሚሹ ዜጎች ቁጥር መበራከቱን የማህበሩ የሰብአዊ መብት ዲፕሎማሲና የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መስፍን ደረጄ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የእርዳታ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን የገለጹ ሲሆን፤ ያለው የማህበሩ ግብዓት ክምችል ባለመጣጠን እርዳታ ለሚሹ ዜጎች ለመድረስ እስቸጋሪ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

እርዳታ ለሚሹ ዜጎች የሚደረገውን ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ  ከማህበሩ ጋር በጋራ ለሚሰሩ የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ መጠየቃቸውን ተገልቷል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply