You are currently viewing እስረኛ ለመጠየቅ በሄዱበት በፖሊስ የታገቱት የባልደራስ አባል አቶ ካሳሁን ደስታ ፍ/ቤት ቀርበው ለተጨማሪ 7 ቀናት ተቀጠረባቸው።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 6 ቀን 2015 ዓ/…

እስረኛ ለመጠየቅ በሄዱበት በፖሊስ የታገቱት የባልደራስ አባል አቶ ካሳሁን ደስታ ፍ/ቤት ቀርበው ለተጨማሪ 7 ቀናት ተቀጠረባቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 6 ቀን 2015 ዓ/…

እስረኛ ለመጠየቅ በሄዱበት በፖሊስ የታገቱት የባልደራስ አባል አቶ ካሳሁን ደስታ ፍ/ቤት ቀርበው ለተጨማሪ 7 ቀናት ተቀጠረባቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 6 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ታህሳስ 3/2015 ዓ.ም በእስር ላይ ለሚገኙት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ስንቅ ለማድረስ በሄዱበት ፖሊስ ያገታቸው አቶ ካሳሁን ደስታ አራዳ ምድብ ግዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ነበር። ፖሊስ እስረኛው ላይ የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እንዳይሰቀልና የክልሉ መዝሙርም እንዳይዘመር ቀስቅሰዋል በሚል ውንጀላ አቅርቦባቸዋል። የተከሳሹ ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ በበኩላቸው፤ ደምበኛቸው የሚባለውን ወንጀል እንዳልፈፀሙና ፖሊስ በባልደራስ አባልነታቸው ብቻ ፓርቲው ላይ ተፅእኖ ለማድረስ እንዳሰራቸው ተናግረዋል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው አቶ ካሳሁን የተያዙት ቀድመዋቸው የታሰሩትን የአቶ ናትናኤል ሁኔታ ለማጣራት እና ስንቅ ለማቀበል በሄዱበት ወቅት ነው። ፖሊስ ሲያስራቸውም ” አንተ የባልደራስ አባል አይደለህ እንዴ?” ብሎ እንደሆነም ገልፀዋል። አቶ ካሳሁን ለፍርድ ቤቱ ፓርቲያቸው ጠቅላላ ጉባኤውን ለማድረግ ዝግጅት ላይ በመሆኑ፤ እሳቸውም እንደ ጉዳይ አስፈፃሚነታቸው ብዙ ጫና ያለባቸውና ፖሊስ አስረብሸዋል ባለበት ሰአት ስራ ላይ እንደነበሩ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በችሎቱ ፖሊስ አቶ ካሳሁን ፍፁም የማያውቋቸው አንድ አዛውንትን የግፍ እስረኛው አባሪ አድርጎ አቅርቧል። ሁለቱ ሰዎች ከዚህ በፊት ፍፁም የማይተዋወቁ ሲሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የተያዩት በዛሬው ችሎት ላይ ነው። ሆኖም ግን ፖሊስ አብረው አመፅ የቀሰቀሱ በማስመሰል አቅርቧቸዋል። ፖሊስ ለቀሪ ምርመራ በሚል ሰበብ 14 ተጨማሪ ቀናትን የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግን የተከሳሹን እና የጠበቃቸውን መከላከያ ከሰማ በኋላ 7 ተጨማሪ ቀናትን ፈቅዷል። በመሆኑም አቶ ካሳሁን በታህሳስ 13/2015 ዓ.ም ፍ/ቤት ይቀርባሉ። አቶ ካሳሁን በአሁኑ ሰአት ከአራዳ ጊዮርጊስ ከፍ ብሎ በሚገኘው 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ (ማዕከላዊ) እንደሚገኙ ፓርቲው አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply