“እስረኞች በመፈታታቸው ኢትዮጵያ በእጅጉ ተጠቃሚ ናት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

ይህን ያደረግነው ለኢትዮጵያ ጥቅም ነው የምንሞተውም የምንኖረውም ለሃገር ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

እስረኞችን ለመፍታት የተገደድነው በሶስት ምክንያቶች ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ፊት ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከፓርላማ አባላት በቅርቡ በምህረት ስለተለቀቁት እስረኞች በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ እስረኞችን የፈታነው በሶስት ምክንያቶች ነው ሲሉም ምላሽ ሰተዋል፡፡

ለዘላቂ ሰላም፤የታሳሪዎችን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ያገኘነውን ድል ለማፅናት እስረኞችን ፈተናል ብለዋል፡፡

ጦርነት አስከፊ ነገር እንደሆነ ከራሳችንም ሆነ ከአለም ታሪክ ተምረናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፡፡

ከህወሃት ጋር በተያያዘም እስካሁን ምንም አይነት ድርድር አልተደገም ሲሉም ምላሽ ሰተዋል፡፡

ነገር ግን ይህ ማለት እስከመጨረሻው ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የውልሰው ገዝሙ
የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply