እስራኤል በአል ሺፋ 90 ታጣቂዎችን መግደሏን አስታወቀች፡፡የእስራኤል ጦር ጋዛ ሰርጥ በሚገኘው በአልሺፋ ሆስፒታል ነበሩ ያላቸውን 90 ታጣቂዎች መግደሉንና በዚያ ባካሄደው አሰሳም ያገኛቸውን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Ecbb3yArq_XUPv9BguHH0kAqQAvNPpgTwkIgFV7sWCVQoMR5JGxo0FmA8EOP3WMVGquizdkyGl3kPHW40SVbgPhDmIyQWOBVCHZUNBFhsOTTR2y4QxQiZL_Duw62nqq3irGtjefCbtx32CLwHafTOI-BiwFYZeGJiFLbN463jqPjt-11XTQlYa7KjwauGFA9AuwoOCMhDAYVFYKCKPDmWe1VGrfkoiq_mBEAcnswXOEBY187bymlSAjIsfbUruegmefa85S1qY4-kShqCQfsferr02dhHlceHa01chSaotjp6NVy2yMR2GPUL5NL_l5HtRze8Mv2JXLQPIb9XjksCQ.jpg

እስራኤል በአል ሺፋ 90 ታጣቂዎችን መግደሏን አስታወቀች፡፡

የእስራኤል ጦር ጋዛ ሰርጥ በሚገኘው በአልሺፋ ሆስፒታል ነበሩ ያላቸውን 90 ታጣቂዎች መግደሉንና በዚያ ባካሄደው አሰሳም ያገኛቸውን 160 ሰዎችን ማሰሩን ትላንት አስታውቋል።

የእስራኤል ጦር ባወጣው መግለጫ ባለፉት ቀናት አሸባሪ ያላቸውን ማስወገድን በሆስፒታሉ አካባቢም የጦር መሳሪያዎች ማግኘቱን ገልጿል።

ጦሩ ሆስፒታሉ እንደገና ታጣቂዎች እንደሚገለገሉበት የሚጠቁም የደኅንነት መረጃዎችን መሰረት በማድረግ በእግረኛና በታንኮች የሚታገዝ ልዩ ኃይል ወደ ስፍራው መላኩን ተናግሯል።

ሀማስ በበኩሉ በሆስፒታሉ ውስጥ የተገደሉት ተዋጊዎች ሳይሆኑ ሰለማዊ ሰዎች ናቸው ሲል አስተባብሏል።

እስራኤል አካባቢውን የወረረችው ሰኞ ማለዳ ነበር ።አል ሺፋ ሆስፒታል ከጦርነቱ በፊት በጋዛ ሰርጥ የሚገኝ ትልቅ ሆስፒታል ነበር እንደ ሮይተርስ ዘገባ።

አሁን ግን በከፊል ስራቸውን ከሚያካሂዱት ጥቂት የጤና ተቋማት አንዱ ሆኗል። ሆስፒታሉ የተፈናቃዮች መጠለያም ነበር ።

የእስራኤል ወታደሮች ለመጀመሪያ ጊዜ በህዳር ወር በሆስፒታሉ ወረራ ካካሄዱ በኋላ በስፍራው ሀማስ ለእዝና ቁጥጥር የሚጠቀምባቸው ማዕከላት ያሉበት ዋሻ ማግኘቱን ተናግሮ ነበር።

ሀማስና የሆስፒታሉ ሐኪሞች ግን ሆስፒታሉ ለወታደራዊ አገልግሎትም ሆነ ለታጣቂዎች መጠለያ ጥቅም ላይ አልዋለም ሲሉ አስተባብለው ነበር።

መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply