
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የአየር ጥቃት መክፈቷ ተነገረ፡፡
የእስራኤል አየር ሃይል ከፍልስጤም ሮኬት መተኮሱን ተከትሎ ጋዛን መደብደብ መጀመሩ ታወቋል፡፡
በትናትናዉ ዕለት የእስራኤል ጦር አሸባሪዎችን ለማደን ነዉ በሚል በዌስት ባንክ በወሰደዉ ጥቃት 11 ዜጎች መገዳለቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡
ይህንንም ተከትሎ ስዴሮትና አሽኬሎን የተሰኙት የአስራኤል ከተሞች የሮኬት ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡
ለሮኬት ጥቃቱ ከፍልስጤም በኩል እስካሁን ኃላፊነተ የወሰደ አካል እንደሌለ አልጄዚራ ዘግቧል፡፡
በዛሬዉ ዕለትም እስራኤል ለሮኬቱ የመልስ ምት ጋዛ ላይ የአየር ጥቃት ከፍታለች ነዉ የተባለዉ፡፡
በአባቱ መረቀ
የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post