እስራኤል በግብጽ የራፋህ መሻገሪያ በኩል ወታደሮቿን ለማሰማራት ማሰቧን አስታወቀች፡፡

የእስራኤል ባለስልጣናት በግብጽ የራፋህ መሻገሪያ በኩል ወታደሮቻቸዉን ማሰማራት የሚችሉበትን ሁኔታ እያጤኑ መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

እስራኤል ይህን ሀሳብ ያመጣችዉ በመሻገሪያዉ በኩል የሃማስ አባላት እንዳያመልጡ እና በጋዛ ያሉ እስራኤላዊያን የጦር እስረኞችን ይዘዉ እንዳይወጡ በማሰብ ነዉ ተብሏል፡፡

በእስራኤል መንግስት እንደ ጥያቄ የቀረበዉ ይህ እርምጃ በግብጽ እና በእስራኤል በኩል ለዉይይት መቅረቡም ተገልጿል፡፡

እስራኤል የሃማስ መሪዎች በራፋህ መሻገሪያ በኩል አድርገዉ ከታጋቾች ጋር ሊያመልጡ ይችላሉ ፤ አምልጠዉም ሊቀበሏቸዉ ወደሚችሉ እንደ ኢራን ፣የመን ወይም ሊባኖስ ያሉ አገራት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮባታል ነዉ የተባለዉ፡፡

በካይሮ ያሉ ባለስልጣናት በበኩላቸዉ በእስራኤል ለተነሳዉ ሀሳብ የሚመለከታቸዉ የግብጽ ኤጀንሲዎች ግዴታቸዉን በአግባብ እና በሃላፊነት እየተወጡ በመሆኑ ምንም ሊያሳስብ የሚገባ ጉዳይ የለም ሲሉ መልሰዋል፡፡

በተጨማሪም ግብጽ በመሻገሪያዉ አከባቢ ያሉ ዋሻዎችን በሙሉ መዝጋቷን ገልጸዋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር
ታህሳስ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply