እስራኤል አዲስ ልውጥ የኮቪድ ዝርያ ማግኘቷን አስታወቀች የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር ቤን-ጉሪዮን ዓለምቀፍ አየር ማረፊያ የደረሱ ሁለት ተጓዦች ላይ አደረግኩት ባለው ምርመራ አዲስ ልውጥ…

እስራኤል አዲስ ልውጥ የኮቪድ ዝርያ ማግኘቷን አስታወቀች

የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር ቤን-ጉሪዮን ዓለምቀፍ አየር ማረፊያ የደረሱ ሁለት ተጓዦች ላይ አደረግኩት ባለው ምርመራ አዲስ ልውጥ ዝርያን ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

የተገኘው ልውጥ ዝርያ እንደዚህ ቀደሞቹ ዝርያዎች አይነት አለመሆኑ መረጋገጡን ፣ነገር ግን ቫይረሱ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የኦሚክሮን እና ዴልታ ዝርያዎች ጋር የሚመሳሰል መሆኑም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በ አዲሱ ልውጥ ቫይረስ የተነሳ እስራኤልን ስጋት እንደገባት አልሸሸገችም ፡፡

ሁለቱ መንገደኞች ወደ እስራኤል እንዴት እንደገቡ ያልተገለፀ ሲሆን በ30ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙ መሆናቸውን የሃገሪቱን መገናኛ ብዙሃን ጠቅሶ አር ቲ ዘግቧል፡፡

አብድልሰላም አንሳር
መጋቢት 09 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply