እስራኤል ኢራን ላይ የበቀል ጥቃት መፈፀሟ ተሰማየእስራኤል ጦር በኢራኗ ኢስፋሃና ግዛት ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል፡፡ከኢራን በተጨማሪም በሶሪያና ኢራቅ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/WgdOAzK9ywblEk3nV0vNaGd3vSNH6Y6LIMnXXOWdKs8r5XLcOFRV91Dj6sacix0DgRj5RBdWkqfJu0xbAK60rwf1pwfow6LzWXHbITzOWycup88LOrXEY-eB6ltJYtMe39kHutMx0uQtyA6IWYyye2m5cWwKkWSgVMtGdfFFoovMWrVaxwCeJYPu0LhCiwhA3wAHOA1NExIgx3OdT2LQ0ZCeSR8K6zQHZ8IfjZiwcidIc7x9i2VIon-k_1lQySGOrCxsF04vUORL2_9sKeWOn31a50Q2J0YEj59p77za2EJLyTNB4oISQ1_DHsDrYGtbvgUf7aq9N58AhXl-CLjCTQ.jpg

እስራኤል ኢራን ላይ የበቀል ጥቃት መፈፀሟ ተሰማ

የእስራኤል ጦር በኢራኗ ኢስፋሃና ግዛት ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል፡፡

ከኢራን በተጨማሪም በሶሪያና ኢራቅ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ እየተሰማ ነዉ ተብሏል፡፡

ኒዮርክ ታይምስ የአሜሪካና የእስራኤል ባለስልጣናት ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበዉ ጥቃቱ በኢራን ወታደራዊ መሰረተ ልማት ላይ ያነጣጠረ ነዉ፡፡

በእስራኤል ሚሳኤል የተመታችዉ የኢራን ከተማም ኢስፋሃን ትሰኛለች፡፡
ኢራን በረራዎችን ማገዷን አስታዉቃለች፡፡

ከኢራን በተጨማሪም በሶሪያና ኢራቅ አካባቢ ፍንዳታዎች እንደተሰሙ ታይምስ ኦፍ እስራኤል በሰበር ዜናዉ እያስነበበ ነዉ፡፡

ይህንን ተከትሎም ኢራን በሶሪያ የሚገኘዉን ጦሯንና የሄዝቦላህን ታጣቂዎች ማስወጣጥ መጀመሯን እየሩሳሌም ፖስት ነዉ የዘገበዉ፡፡

የቀጠናዉ ሀገራትም ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ወድቀዋል፡፡

በእስራኤል ገሊላ አካባቢ የሳይረን ድምጽ ሌሊቱን ተሰምቷል ቢባልም የእስራኤል ጦር ግን ሃሰት ነዉ ብሏል፡፡
እስራኤል ተጨማሪ ጥቃቶችን በኢራን ላይ እንደምትወስድ አስታዉቃለች፡፡

ኢራንን በበኩሏ የመልስ ምቴ ከባለፈዉ እጅግ የከፋ ነዉ ስትል ማስጠንቀቂያ እየሰጠች ነዉ፡፡

አባቱ መረቀ
ሚያዚያ 11ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply