እስራኤል ደቡብ ሊባኖስን ደበደበች

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-5725-08dbc857f302_cx0_cy10_cw0_w800_h450.jpg

የጸጥታው ምክር ቤት ሐማስን እንዲያወግዝ የእስራኤል አምባሳደር ጠየቁ

ታጣቂዎች፥ በድንበር በኩል ሰርገው ገብተዋል፤ በሚል፣ እስራኤል፣ ዛሬ ሰኞ፣ የደቡብ ሊባኖስ የድንበር አካባቢን በከባድ መሣሪያ ደብድባለች፡፡

በሊባኖስ የሚገኘውና በኢራን የሚደገፈው ሔዝቦላህ በበኩሉ፣ ድንበር ጥሶ ገብቷል፤ የሚለውን ክስ አስተባብሏል። ከእስራኤል ጋራ ግጭት አለ፤ የሚለውንም አጣጥሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእስራኤል አምባሳደር፣ የጸጥታው ም/ቤት ሐማስን እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።

“የሐማስ የጦር ወንጀል በማያሻማ መንገድ ሊወገዝ ይገባል፤” ሲሉ ተደምጠዋል አምባሳደሩ ጊላድ ኤርዳን።

የጸጥታው ም/ቤት፣ ትላንት ምሽት ዝግ ስብሰባውን ከማድረጉ በፊት፣ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት አምባሳደሩ፣ “እስራኤል አፋጣኝ ድጋፍ ሊሰጣት ይገባል፤” ሲሉም አክለዋል።

አምባሳደሩ የሐማስን የቅዳሜ ድንገተኛ ጥቃት፣ እ.አ.አ በ2001 አል ቃዒዳ በአሜሪካ ምድር ላይ ከፈጸመውና ሦስት ሺሕ የሚጠጋ ሕይወትን ከቀጠፈው ጥቃት ጋራ አመሳስለውታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply