እስራኤል ጦርነት ዉስጥ ብትሆንም የጥምቀት በዓል እንደማይስተጓጎል የሀገሪቱ መንግስት አስታወቀ፡፡የጥምቀት በዓልን በእስራኤል ለማክበር በቂ የፀጥታ ዝግጅት ማድረጉን የሀገሪቱ መንግስት…

እስራኤል ጦርነት ዉስጥ ብትሆንም የጥምቀት በዓል እንደማይስተጓጎል የሀገሪቱ መንግስት አስታወቀ፡፡

የጥምቀት በዓልን በእስራኤል ለማክበር በቂ የፀጥታ ዝግጅት ማድረጉን የሀገሪቱ መንግስት ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በድምቀት የሚከበረዉ የጥምቀት በዓል በእስራኤል እንዲከበር በቂ የፀጥቻ ዝግጅት መደረጉን የሀገሪቱ ኢምባሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጧል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አድማሱ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤በሀገሪቱ የሚገኙ የዕምነቱ ተከታች በዓሉን በሰላም እንዲያከብሩ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡

እስራኤል ምንም እንኳን በጦርነት ዉስጥ ብትሆንም በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የፀጥታ ኃይሉ ዝግጅቱን አጠናቋል ነዉ ያሉት አምባሳደሩ፡፡

ወደ እስራኤል ሀገር ሄደዉ መንፈሳዊ በዓላትን ማክበር ለሚፈልጉ ሰዎች በሩ ክፍት መሆኑንም አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡

በቅርቡም የእስራኤል መንግስት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር ዉይይት ማድረጉን አምባሳደር አለሊ አድማሱ አስታዉሰዋል፡፡

የሃማስን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ የከፈተችዉን ጦርነት አጠናክራ እንደምትቀጥል በመግለጽ ላይ ነች፡፡

አባቱ መረቀ

ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply