እስራዔል በሁለት ዓመት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ምርጫ ልታካሂድ ነው

እስራዔል በሁለት ዓመት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ምርጫ ልታካሂድ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል በሁለት ዓመት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ወደ ጠቅላላ ምርጫ ልታመራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ምርጫው የሚካሄደው መንግስቱን የመሰረቱት ሁለቱ ፓርቲዎች በበጀት ጉዳይ ላይ ባለመስማማታቸው ነው ተብሏል፡፡

መራጮች ከ12 ወራት በኋላ በመጋቢት ወር ዳግም ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እንደሚያቀኑ ነው የተገለጸው፡፡

ይህን ተከትሎም የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሊኩይድ ፓርቲ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ቤኒ ጋንትዝ ፓርቲ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ሁለት ምርጫዎች አሸናፊ ባለመኖሩ መንግስቱን የመሩት በጥምረት እንደነበር ይታወሳል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትርነቱንም ቦታ በፈረንጆቹ ህዳር ወር 2021 ቤኒ ጋንትዝ እንደሚይዙት ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር ይታወቃል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post እስራዔል በሁለት ዓመት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ምርጫ ልታካሂድ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply