እስር ላይ የነበሩት የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር ተለቀቁ።እስክንድር ነጋን ጨምሮ ታስረው የነበሩ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት ከእስር…

እስር ላይ የነበሩት የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር ተለቀቁ።

እስክንድር ነጋን ጨምሮ ታስረው የነበሩ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት ከእስር መለቀቃቸው ተሰምቷል።

የፓርቲውን ሊቀመንበር እስክንድር ነጋን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮልና በእስር ላይ የነበሩት የፓርቲው አመራሮች ከእስር መፈታቸውን ፓርቲያቸው በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።

እንዲሁም ከእስር እንዲወጡ የተወሠነላቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ( ኦፌኮ) አመራሮች ጃዋር መሃመድ ፣በቀለ ገርባ ከእስር ቢለቀቁም፣ ቀኑ በመምሸቱ ምክንያት ዛሬ አንወጣም ማለታቸውም ተሠምቷል።

ታህሳስ 29 ቀን፣ 2014 ዓ.ም

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply