እስከ ህዳር 30 በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ ያልተመዘገቡ የንግዱ ማህበረሰብ በማንኛውም ግዥ መሳተፍ አንደማይችሉ ተገለፀ

ኹሉም የንግዱ ማህበረሰብ በሥርዓቱ ካልተመዘገቡ መጫረትም ሆነ ግዥ መፈጸም አይችሉም ተብሏል

ማክሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) እስከ ህዳር 30 በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ ያልተመዘገቡ የንግዱ ማህበረሰብ በማንኛውም ግዥ መሳተፍ እንደማይችሉ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አሰታወቀ።

የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

የምክክር መድረኩን ንግግር በማድረግ የከፈቱት የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃጂ ኢብሳ እንደገለጹት፣ ሥርዓቱ የኢትዮጵያ የግዥ አሰራር ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ የግዥ ሥርዓት የሚያሸጋግር ነው።

ኹሉም የንግዱ ማህበረሰብ እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 በሲስተሙ ተመዝግበው መጠቀም ይኖርባቸዋል። ካልሆነ መጫረትም ሆነ ግዥ መፈጸም አይችሉም።

የንግዱ ማህበተሰብ በአለም ላይ አገር ይመራል፣ ስለሆነም መዘመን ይኖርበታል። በአደጉ አገሮች የንግዱ ማህበረሰብ ዘመናዊ የግዥ ሲስተም በመከተል ይባክን የነበረውን ጊዜና ገንዘብ ቀጥበዋል።

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሚበጀተው በጀት 70 በመቶ ለግዥ የሚውል በመሆኑ የግዥ ሥርዓታችን መዘመን መቻል አለበት። ካልሆነ በርካታ የህዝብ ሀብት ይባክናል። የኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ በኢትዮጵያ እንጅ በበርካታ አገራት የተለመደና የቆየ የግዥ ስርዓት ነው። ከምንም በላይ ብልሽ አሰራርን በማስተካከል ይሰረቅ የነበረውን የአገር ሀብት ያድናል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ሙሉ ለሙሉ የወረቀትን ወጭን ይቀንሳል፣ የትራንስፖርት ወጭን በማዳን በኹሉም ቦታ ያሉ ተወዳዳሪዎችን በእኩል ማወዳደር የሚችል ሲስተም መሆኑን ገልጸዋል።

ሲስተሙን በመጠቀም እንዴት መጫረት፣ ውል መያዥ፣ ፎርም መሙላት እንደሚቻል ማብራሪያ እየተሰጠ ሲሆን፤ በቀጣይ ከንግዱ ማህበረሰብ አስተያየት እንደሚሰጥበትም ተገልጿል።

The post እስከ ህዳር 30 በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ ያልተመዘገቡ የንግዱ ማህበረሰብ በማንኛውም ግዥ መሳተፍ አንደማይችሉ ተገለፀ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply