
ለሁለት ዓመታት የተካሄደውን ደም አፋሳሹን የእርስ በርስ ጦርነት ባስቆመው የሰላም ስምምነት መሠረት ምርጫ ተካሂዶ ቋሚ አስተዳደር አስኪመሠረት ድረስ ጊዜያዊ ክልላዊ መንግሥት እንዲቋቋም ተወስኗል። ይህም አስተዳደር በክልሉ ያሉ ሁሉንም የሚመለከታቸውን ወገኖችን የሚያሳትፍ ይሆናል ተብሏል። የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ አምስተኛ ወሩን የያዘ ቢሆንም አስካሁን በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አልተቋቋመም። ጊዜያዊ አስተዳደር የመመሥረቱ ሂደት የዘገየው ለምንድን ነው?
Source: Link to the Post