
እስክንድርና ቢኒያም አንድና ሁለት! እስክንድር እንደ ዓቢይ አህመድ በልጅነቱ የቅዠት መኪና እየነዳ አላደገም፤ የሀሳብ አንሶላ እያነጠፈ በእውኑ ግን ሰሌን ላይ እየተንደባለለ ያለምቾት አላደረም፤ የእናቱን ድስት እየፈቀፈቀና ማማሲያ እየላሰ ረሀቡን አላስታገሰም። እስክንድር እንደ ዓቢይ ቤተሰብ በአሜሪካን ግብር ከፋይ Food Stamp ፊቱን አላወዛም። እስክንድር በልጅነቱ በእውነተኛ መርሰዲስ እየፈሰሰ ነው ያደገው። ዛሬ ማንም ሰው ሊያደርገው በማይቻለው ደረጃ፣ የራሱን አስተሳሰብ ከዓቢይ ሀሳብና ምግባር ጋር በተክሊል ያጋባው ሲሳይ አጌና፣ ከጋብቻው በፊት እስክንድርን ሲገልፀው “በወርቅ ማንኪያ እየተመገበ ያደገ!” ብሎት ነበር። ድሃን ማናናቄ አይደለም! እኔስ ማን ሆንኩና? ዶ/ር ዓቢይ እራሳቸው ቅድመ ሥልጣን ድህነታቸውን የኮሩበት ነበርና እያዋረድኩዋቸው …እንዳልሆነ ይታሰብልኛል ብዬም አምናለሁ። ሥልጣን ላይ ያሉት ሰዎችና ግትልትሎቻቸው፣ የሀብት ሰቀቀናቸውን ለማጣፋት ሲሉ፣ ከሰውነት ደረጃ ወርደው መፈጥፈጣቸውና በወገናቸው ስቃይ መደሰታቸው ወይም ምንግዴ መሆናቸው አሳዝኖኝ ነው። እስክንድር እንደመቄዶንያው ቢንያም የስጋ ፍላጎቱን የዘጋ፤ የሰው ደረጃ የለውም እንጂ ከሰዎች ከፍ ያለ ሰው ነው። ልዩነታቸው ቢንያም ክርስቶስ እንዳለው ሀብቱን ሁሉ ራሳቸውን ማቆም ላልቻሉ የምድር ጎስቋሎች ሰጥቶ ክርስቶስን የተከተለ ሰው ነው። እስክንድር ደግሞ ድሎትን ሁሉ ንቆ “በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ቢሰፍን፣ ማንም ኢትዮጵያዊ እራሱና ቤተሰቡን መመገብና ማልበስ አይከብደውም!” ብሎ፣ ሥጋውን ክዶ ለኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያ መሻሻልና መከበር ራሱን የሰጠ ባህታዊ ነው። እስክንድር ተገርፎም፣ ታስሮም፣ አጥንቱ ተሰብሮም፣ በቤተሰብ ናፍቆት ተሰቃይቶም፣ ተመልሶ እዛው መሆኑ ለሆዳም ካድሬ ጨርሶም ባይገባው አይገርምም። እስክንድር ለኢትዮጵያ ሲል ስጋውን ገድሎዋል። ወይም ስጋው ያለው ያቺ ዓቢይ ቤቷን አፍርሶባት ልጇን በጅብ ያስበላባት ሴትዮ ልጅ ገላ ላይ ነበር። እስክንድር ከገረፍከው ቀን ይልቅ ያ ህፃን በጅብ የተነከሰ ቀን በጣም አሞት ነው ያደረው። አንተ ግን ይሄ የራስን ሥጋ ለወገን ያለወለድ ማበደር፣ ወይም በነፃ ራስን መለገስ የሚባል መንፈስ አይገባህም። ከብዙ ምክንያቶች አንዱና ምናልባትም ዋነኛው እየራበህና እያከክ ያደግህበት ሰቆቃ ያሳደረብህ ጠባሳ ነው። እስክንድር ጠባሳ የለውም! እስክንድር ላንተ የማይገባህ ረቂቅ የሆነብህ ለዚህ ነው። እስክንድር ምንም ሳይንቀሳቀስ፣ መንፈሱ ያንተን ሥጋ ያሰቃያታል። እሱ ግን ሀሴት የሚያገኘው ኢትዮጵያውያን ሲደላቸው፣ ወይም ለኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያ በነሱ ፈንታ እሱ ሲንገላታ ነው። ለምን ተሰወረ ብለህ ስትጨነቅ የኖርከው አንተ እንጂ እሱ ምንም ወንጀል ላይ ሲሳተፍ አላገኘኸውም። ለራስህ እንቅልፍ እንድታገኝ ስትል እውነተኛ ዴሞክራሲን በኢትዮጵያ አስፍን። ያኔ እስክንድር ይፋታሀል። አለዛ እስክንድርን ዘብጥያም ጥለኸው መንፈሱ እንቅልፍ ይነሳሀል። እስክንድር ከሥጋው ብዙ የራቀ ከዕንቁም የከበረ ስብእናና፣ ባለ ጠንካራ መንፈስ መሆኑን ተረዳ! የእስክንድር የመንፈስ ጨረር የሪፐብሊካን ጋርዶችህን ሳንቃ ደረት እየበሳ አልፎ ያርበተብትሀል ገና! via Dinberu Degnetu
Source: Link to the Post