እስክንድር ነጋ እና ሌሎች የባልደራስ አመራሮችን ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ጥር 1 (ከጃኑዋሪ 9) ጀምሮ ሊካሄድ እንደሆነ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28…

እስክንድር ነጋ እና ሌሎች የባልደራስ አመራሮችን ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ጥር 1 (ከጃኑዋሪ 9) ጀምሮ ሊካሄድ እንደሆነ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28…

እስክንድር ነጋ እና ሌሎች የባልደራስ አመራሮችን ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ጥር 1 (ከጃኑዋሪ 9) ጀምሮ ሊካሄድ እንደሆነ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለአንድ ወር የሚቆየው ይህ የባልደራስ አመራሮችን የማስፈታት ዘመቻ የፊርማ ማሰባሰብ፣ በታዋቂ ኢትዮጵያውያን የሚፃፍ ለጠቅላይ ሚንስትሩ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሚላክ ግልፅ ደብዳቤን እንደሚያካትት ተገልጧል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን እና ዓለም አቀፍ መንግስታትን የሚያካትት ተፅእኖ ፈጣሪ እንቅስቃሴ ይደረጋል ተብሏል። ይኸውም እንደ ትዊተር እና ፌስቡክ ባሉ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚተላለፉ የመልዕክቶች ዘመቻ፣ እንዲሁም በተመረጡ የዓለም ከተሞች የሚካሄዱ ትዕይንተ ህዝቦችን እንደሚጨምር ነው ከዓለም አቀፍ ግብረ ኃይል አስተባባሪዎች የተገኘ መረጃ ጠቁሟል ኢትዮ ኒውስ የዘገበው። የፊታችን ቅዳሜ በዙም በሚካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተለመደ ተሳትፏቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply