እሹሩሩ የስልጠና ማዕከል በሞግዚትነት ያሰለጠናቸዉን 120 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡ለትርፍ የተቋቋመዉ እሹሩሩ የሞግዚትነት ድጋፍ እና ስልጠና ሰጭ ማእከል፣ 120 ለሚሆኑ ከስደት ተመላሾች ከአይ…

እሹሩሩ የስልጠና ማዕከል በሞግዚትነት ያሰለጠናቸዉን 120 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

ለትርፍ የተቋቋመዉ እሹሩሩ የሞግዚትነት ድጋፍ እና ስልጠና ሰጭ ማእከል፣ 120 ለሚሆኑ ከስደት ተመላሾች ከአይ ኦ ኤም/ IOM/ ጋር በመተባበር የሞግዚትነት ስልጠና እንደተሰጣቸዉ የድርጅቱ መስራችና ማኔጅንግ ዳይሬክተር ሰለሞን ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡
አቅም ለሌላቸዉ 20 ለሚሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናዉ በነጸ እንደተሰጣቸዉም ገልጸዋል፡፡

ማኔጅንግ ዳይሬክተሩ አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ ድርጅቱ ከተቋቋመ በ 9 አመት ዉስጥ አስካሁን ከስምንት ሽህ አንድ መቶ በላይ ሰልጣኞችን አሰልጥኖ በማስመረቅ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናግረዋል፡፡

ለሁለት ወር በነበራቸዉ የስልጠና ጊዜ የልጆች አስተዳደግ እና አያያዝ፤ ስነ ልቦና ከመገንባት አንጻር እንዲሁም ከአሰሪዎቻቸዉ ጋር ሊኖራቸዉ ስለሚገባ ተግባቦት ጋር በተገናኘ በቂ ስልጠና እንዳገኙም ነግረዉናል፡፡

እሽሩሩ የስልጠና ማእከል ይህን መሰል ስልጠና ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራዉ ከመካከለኛዉ ምስራቅ ከስደት የተመለሱ ሴቶች ላይ በመሆኑ ስልጠናዉ የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ ፤እናቶች ከወሊድ በኋላ ረዘም ላሉ ጊዜያት ከስራ ገበታ እንዳይርቁ ያደርጋቸዋል ነዉ ያሉት፡፡

በተጨማሪም የበርካታ ዲፕሎማቶች መቀመጫ ለሆነችዉ አዲስ አበባ መልካም ገጽታ ከመገንባት አንጻር ስልጠናዉ ጠቃሚ መሆኑም ተነግሯል፡፡

እንደ ሀገርም የህገ-ወጥ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑ የተነገረለት የስልጠና ማእከሉ፣ በሞግዚትነት አሰልጥኖና በሙያ ብቃትና ምዘና ተመዝነዉ ወደ ስራ ያስገባቸዉ ሰልጠኞች ከ4,500 እስከ 5,000 ባለዉ ደመወዝ በድርጅቱ ስር በማስቀጠር ወደስራ እንደሚያስገባቸዉ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply