“እባካችሁ መንግስትና ያገባናል የሚሉ ወገኖች ሁሉ እንዲደርሱልን ድምጻችን አስተላልፉ!” ባለቤቱን፣ልጁንና ሰራተኛውን በጉምዝ ታጣቂዎች በኩጅ ቀበሌ የተነጠቁት አባት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

“እባካችሁ መንግስትና ያገባናል የሚሉ ወገኖች ሁሉ እንዲደርሱልን ድምጻችን አስተላልፉ!” ባለቤቱን፣ልጁንና ሰራተኛውን በጉምዝ ታጣቂዎች በኩጅ ቀበሌ የተነጠቁት አባት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጅ በተባለው ቀበሌ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ የጉምዝ ታጣቂዎች “ቀዮችን በሏቸው” በማለት በዋናነት የአማራን በተጨማሪም የኦሮሞ፣የሺናሻና ሌሎች ብሄር ተወላጆችን በጅምላ እያሰቃዩ መግፈላቸው ይታወቃል። የመንግስት መዋቅር በሚደግፈው በቡድን የጦር መሳሪያና በስለት በታገዘው ጭፍጨፋም ቢያንስ ከ207 በላይ ሰዎች መገደላቸው የክልሉ መንግስት ያመነው መረጃ አመልክቷል። የዘር ፍጅቱን አሰቃቂነት ኢሰመኮና ኢሰመጉ ያወጡት ቅድመ ሪፖርት እንዳለ ሆኖ የመንግስት አካላትም ሆነ ከጥቃቱ የተረፉ ተፈናቃዮች በየቀኑ እያጋለጡት ይገኛል። ከጥቃቱ ያመለጡ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በሌሊት ጫካ አቆራርጠው ድባጤ ወረዳ እና ቡለን መድረሳቸውን በመግለፅ አስፈላጊው ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው መጠየቁ ይታወሳል። ይሁን እንጃ በኩጅ ቀበሌ 3 ቤተሰባቸውን በጨካኞች የተነጠቁት አቶ እንዳለው አዳሜ አሁንም ድረስ እርዳታ የሚያደርስ የመንግስት አካል ባለመገኘቱ የችግሩ ስፋት አሳሳቢ እየሆነ ነው ብለዋል። እባካችሁ በፈጣሪ ፍቃድ ከጥይትና ከስለት ያመለጡ ሰዎች በተለይም ህጻናት፣ሴቶችና አቅመ ደካሞች በርሃብ እንዳይጎዱብን የሞመለከተው አካል እንዲደርስልን ድምጻችን አስተላልፉልን ሲሉ ተማፅነዋል። በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ሆነንም ዋስትና የለንም ያሉት አቶ እንዳለው መንግስት የጅምላ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ ባሉ ነፍሰ ገዳዮች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ፣ ተባባሪ አመራሮችን በቁጥጥር ስር በማዋል፣ተፈናቃዮችን በማፅናናትና መልሶ በማደራጀት እንዲክሰን ብሎም ካለንበት የመከራ ህይወት እንዲታደገን እንፈልጋለን ብለዋል። ከፌደራል መንግስት በተጨማሪ ሁሉም የክልል መንግስታት አስፈላጊውን ሰብአዊ ድጋፍ እንዲያቀርቡላቸው ነው በተፈናቃይ ወገኖች የተጠየቀው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply