እነ አብይ አህመድ መርዶ እየዘነበባቸው ነው። አሜሪካ በዚህ መልኩ ፈፅም ያለችውን ሁሉ ሲተገብር የኖረው፣ የአብይ አህመድ መንግስት ዛሬ ደሞ ከነጩ ቤተ መንግስት፣ በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ለምስራቅ አፍሪካ ጭምር አደጋን የደቀነ ስለሆነ የጣልኩትን ማዕቀብ ለአንድ አመት አራዝሚያለሁ ብላ፣ ክው አድርጋዋለች። ከዚህም ባሻገር በአማራ ክልል ማጀቴ ላይ የአብይ ወታደር 70 ንፁሀን አማራዎችን በግፍ መግደላቸውን ከ10 ሚሊየን በላይ የTwitter ተከታይ ያለው ታዋቂው መፅሄት ዘጋርዲያን አጋልጧል። እነ አብይ አህመድ በአማራ ክልል ውስጥ ከኢትዮዽያም አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ ጭምር አደጋ የደቀነ ጦርነት እያካሄዱ እንደሆነ አሜሪካ ዛሬ አጋልጣለች። በተቃራኒው፣ አብይ አህመድና ሙርከኛው ብረሀኑ ጅላ ደመሰስነው ቀጠቀጥነው ያሉት ፋኖ የማይቀመስ እንደሆነ አለ…ም እየመሰከረ ነው። ሚኒሻው አበበ አረጋ ክልሉ ሰላም ነው ያለው ትናት ቢሆንም ዛሬ የኢትዮዽያ ህዝብ በመንግስት የተደበቀውን ሀቅ ከሌላ አገር መንግስት እየሰማ ነው። ይሄ አውርቶ አደር መንግስት በውሸት እያምታታ ህዝብ የሚያሰቃይበት ገመዱን በዲፕሎማሲም በመሬት ውጊያም እየተበጣጠሰ ነው። እናም ወገኔ ይልቅ ከአራቱም መአዘን ፊትህን 4ኪሎ ላይ ደቅነህ ተራመድ። እመነኝ ይሄ መንግስት መልሶ መንግስት እንደማይሆን በአለቆቹ ሁሉ ተመስክሮበታል። የመከራ ግዜን ከማራዘም ውጭ አብይ አህመድ መሪ ሆኖ የሚቀጥልበት እድሉ ሁሉ አብቅቷል። የሽግግር መንግስትህን ለማቋቋም በየ አካባቢህ ያለውን የፒፒ ነገዴ አባረህ አራት ኪሎን እየጠራህ ገስግስ። መከላከያ ሆይ አሁንስ ለማን እንደምትሞት አልገባህም ይሆን..? አሁንም አልመሸም አፈሙዝህን ወደ አስገዳይ አዙረህ አገርህን ታደግ። እመነኝ ይሄ መንግስት አብቆተለታል። ይህ የጌታቸው ረዳ ንግግ መዝሙር መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል። ይህ የትልቁ የአማራና የኢትዮዽያ ህዝብ ብሎም የዲፕሎማቶቹ የተረጋገጠ ጥሬ ሀቅ ነው። ወደፊት ሆኖ ስታየው ትንቢት እንደሰማህ ከምትገረም አሁን እጅህ ላይ ያለውን እድል ተጠቅመህ የታሪክ ባለቤት ሁን። Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ ለአዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- //Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng //https://www.facebook.com/asharamedia24 //ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedi
Source: Link to the Post