You are currently viewing እነ እስክንድር ነጋ እና ጠበቆች በአቃቢ ህግ ምስክር ላይ እያቀረቡት ያለው የመስቀለኛ ጥያቄ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፤ ለማጠናቀቅ ባለመቻሉም ለፊታችን ማክሰኞ እንዲቀጥል ሲል ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ…

እነ እስክንድር ነጋ እና ጠበቆች በአቃቢ ህግ ምስክር ላይ እያቀረቡት ያለው የመስቀለኛ ጥያቄ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፤ ለማጠናቀቅ ባለመቻሉም ለፊታችን ማክሰኞ እንዲቀጥል ሲል ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ…

እነ እስክንድር ነጋ እና ጠበቆች በአቃቢ ህግ ምስክር ላይ እያቀረቡት ያለው የመስቀለኛ ጥያቄ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፤ ለማጠናቀቅ ባለመቻሉም ለፊታችን ማክሰኞ እንዲቀጥል ሲል ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል ጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ አሁን ላይ አሸባሪ ተብሎ በተፈረጀውና በአማራ፣በአፋር ብሎም በኢትዮጵያ ላይ ይፋዊ ጦርነት በከፈተው በትሕነግ መራሹ ስርዓትና መንግስት ለበርካታ ዓመታት በእስር ተሰቃይተዋል። ኢህአዴግን በብዕራቸው በሰላማዊ መንገድ በእጅጉ ከታገሉትና በመጨረሻም የትሕነግ የሽብር ቡድን ከቤተ መንግስት ወጥቶ ወደ መቀሌ እንዲመሽግ ካደረጉት መካከል አንዱ ስለመሆናቸው ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል፤ “ድል ለዲሞክራሲ!” በሚል ንግግራቸውም ይታወቃሉ _ጋዜጠኛ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹና የባልደራስ መስራችና ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ። ከፈታኙ የትግል ቆይታ በኋላም አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በአዲስ አበባ መገደሉን ተከትሎ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩምና አስካለ ደምሌ ይገኙበታል። እነ እስክንድር ነጋ በግፍ የታሰሩ የሕሊና እስረኞች በመሆናቸው ሊፈቱ ይገባል በማለት ባልደራስ በማህበራዊ ሚዲያ ተደጋጋሚ የይፈቱ ዘመቻ ማካሄዱና ለተለያዩ ተቋማትም በደብዳቤ መግለጹ ይታወቃል። አነጋጋሪ የነበረውና ብዙ ጊዜ ያከራከረው የአቃቢ ሕግ ምስክሮች በዝግ እና ከመጋረጃ በስተጀርባ ይመስክሩልኝ የሚለው ጥያቄ በክርክር ውድቅ ተደርጎ በግልጽ ችሎት የአቃቢ ህግ ምስክር መሰማት የጀመረው ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ/ም ነው። እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ድረስ 6 የአቃቢ ህግ ምስክሮች የተደመጡ ሲሆን ሁሉም በሚባል አግባብ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ትኩረት አድርገው የምስክርነት ቃል መስጠታቸው ታውቋል። ምስክርነታቸውን ከሰጡት መካከል ለረዥም ጊዜ በእስር ላይ የቆዬ እና ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ በእስር ላይ እያሉ የግድያ ሙከራ አድርጎባቸዋል የተባለው አቶ ፈንታሁንን/ይባስን ጨምሮ ሌሎች የአቃቢ ህግ ምስክሮች መስክረዋል። አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩምና አስካለ ደምሌ ከቂሊንጦ እና ቃሊቲ ማ/ቤት ቀርበዋል። የአቃቢ ህግ ምስክር ሆኖ በመቅረብ ቃሉን የሰጠው አቶ ወርቁ በተከሳሾች፣በጠበቆቻቸውና በዳኞች በኩል በርካታ መስቀለኛ ጥያቄዎች የቀረቡለት መሆኑን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በችሎት ተገኝቶ ተመልክቷል። ምስክሩ ከተከሳሾችና ከጠበቆች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች በበቂ ምላሽ ሲሰጥ አልተስተዋለም፤ እንዲያውም ችሎቱንና ታዳሚዎችን ጭምር ግራ የሚያጋባና ብዙዎችን ፈገግ ያደረገና ያነጋገረ ምላሽ ሲሰጥ ተደምጧል። ባልደራስ በአዲስ አበባ ህገ ወጥ የመሬት ወረራን፣ መንግስታዊ የመኖሪያ ቤት ፈረሳንና ሌሎችንም ጉዳዮች በተመለከተ በማውገዝና በመታገል ረገድ የሄደበትን ርቀት አመላካች ምላሽ ሰጥተዋል። ከጠዋት እና ከሰዓት የቀጠለው የመስቀለኛ ጥያቄ ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ ችሎቱ ለፊታችን ማክሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ችሎቱን ለመታደምም የተከሳሽ ቤተሰቦችን ጨምሮ፣ የባልደራስ አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ጋዜጠኞችና አድናቂዎቻቸው በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት የችሎት አዳራሽ መገኘታቸውን ተመልክተናል። በመጨረሻም እነ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩምና አስካሌ ደምሌ የችሎት ታዳሚዎችን በማመስገንና በማበረታታት፣ “እውነት ያሸንፋል!” በማለት ተሰናብተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply