እነ እስክንድር ነጋ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የሚጠይቀውና ለአንድ ወር የሚቆየው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ ነገ እንደሚጀምር ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 30 ቀን 2013…

እነ እስክንድር ነጋ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የሚጠይቀውና ለአንድ ወር የሚቆየው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ ነገ እንደሚጀምር ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2013…

እነ እስክንድር ነጋ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የሚጠይቀውና ለአንድ ወር የሚቆየው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ ነገ እንደሚጀምር ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለአንድ ወር ይደረጋል የተባለው እነ እስክንድር ነጋን፣ስንታየሁ ቸኮልን፣አስቴር ስዩምንና አስካለ ደምሌን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለማስፈታት ተፅዕኖ ለመፍጠር ያለመው ሁሉንአቀፍ ዘመቻ በርካታ ተግባራት ተካተውበታል። ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድና ለአለም አቀፍ ተቋማትና ለሌሎች ባለስልጣናት ግልፅ ደብዳቤ መጻፍን፣ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን፣የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ማካሄድንና የመሳሰሉት ተግባራት ይከናወኑበታል ተብሏል። ይህን ፍትህ የመጠየቅ ዘመቻ የሚመራው አለም አቀፍ ግብረ ሀይል መዋቀሩ የተነገረ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ዘመቻውን እንደሚመራውና ስለዘመቻውም በዙም መግለጫ እንደሚሰጥበት ባልደራስ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply