You are currently viewing እነ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እና ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው 6 ሰዎች ለግንቦት 16 ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ተቀጥረዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)    ግንቦት 2/2015 ዓ/ም       አዲስ…

እነ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እና ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው 6 ሰዎች ለግንቦት 16 ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ተቀጥረዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 2/2015 ዓ/ም አዲስ…

እነ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እና ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው 6 ሰዎች ለግንቦት 16 ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ተቀጥረዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 2/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ እነ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እና ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው 6 ሰዎች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ግንቦት 1/2015 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው መዝገቡ ለይደር በተቀጠረው መሰረት ግንቦት 2/2015 ከሰዓት ተገኝተዋል። በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረቡት 6 ሰዎችም፦ 1) ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ 2) ፕ/ር ማዕረጉ ቢያበይን፣ 3) መ/ር ሄኖክ አዲሴ፣ 4) ሰለሞን ልመንህ፣ 5) መ/ር ንዋይ ዮሃንስ እና 6) ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ናቸው። ፌደራል ፖሊስ “የሽብር ድርጊት ተግባር በመፈጸም በንጹሃን ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሳቸው በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው” በእስር ላይ ስለመሆናቸው ገልጧል። ጎበዜ ሲሳይ ጋዜጠኛ ስለሆነ የተጠረጠረበት ወንጀልም ከሚዲያ ጋር የተያያዘ ስለሆነ ጉዳዩ ሊታይ የሚገባው በመደበኛ ወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህጉ ሳይሆን በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ 1238/2013 አንቀጽ 86 (1) መሰረት ነው በሚል በጠበቆች ለቀረበው ጉዳይ ዳኛ በዝምታ በማለፍ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ጊዜ በመፍቀድ ለግንቦት 16/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ስለ መስጠቱ ጠበቃ አዲሱ አልጋው ለአሚማ ተናግሯል። ጠበቃ ታለማ ግዛቸው መንግስት ያለ ወንጀላችን ስም በመስጠት ዶክሜንታሪ በመስራት ወንጅሎናል ለሚለው የእነ ፕ/ር ሲሳይ ቅሬታ ተጠርጣሪ ነው ወንጀለኛ እስካላለ ድረስ ዳኛ ትክክል ነው የሚል ምላሽ ስለመስጠቱም ገልጸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply