እነ ፋኖ ሻለቃ ደረጀ በላይ እና ፋኖ ሻለቃ አይሸሹም ዮሃንስ ከአባላቶቻቸው ጋር ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባብል ተደረገላቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም…

እነ ፋኖ ሻለቃ ደረጀ በላይ እና ፋኖ ሻለቃ አይሸሹም ዮሃንስ ከአባላቶቻቸው ጋር ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባብል ተደረገላቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ እነ ፋኖ ሻለቃ ደረጀ በላይ እና ፋኖ ሻለቃ አይሸሹም ዮሃንስ ከአባላቶቻቸው ወደ ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩ አቡሃይ እንተደተናገሩት ፋኖ ሻለቃ ደረጀ በላይ እና ፋኖ ሻለቃ አይሸሹም ዮሃንስ ከአባላቶቻቸው ጋር እንዲሁም ከመከላከያ እና ከአማራ ልዩ ሃይል ጋር በመሆን አኩሪ ድል የፈፀሙ መሆኑን በመግለጽ ጦርነቱ ተጀመረ እንጅ አልተጠናቀቀም ብለዋል፡፡ በቀጣይ የትግራይ ወራሪ ሃይል እስኪ ደመሰስ ድረስ ትግላችሁን አጠናክራቸሁ እንድትቀጥሉ ሲሉም አሳስበዋል፡፡ ፋኖ ሻለቃ ደረጀ በላይ ለመከላከያ፣ ከአማራ ልዩ ሃይል፣ ለሚሊሻና ለአማራ ፋኖ ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል፤ ትግላችን ገና አልተጠናቀቀም፤ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡ ሻለቃ አይሸሹም ዮሃንስ በበኩላቸው እኛ አሁን ከእዚህ ደረጃ የደረስነው በህዝባችን ሃይል ነው፤ ትግላችን ገና ከዚህ በላይ ይቀጥላል፤ ሁላችንም አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ለማዳን አንድ ልንሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡ በእለቱም ለፋኖ አባላት የሽልማት ስነ- ስርዓት የተደረገላቸው ስለመሆኑ የጎንደር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ዘገባ አመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply