እናት ወተት እና የወተት ተዋፅኦ ማቀነባበሪያ አርቲስት ራሄል እንግዳን በብራንድ አምባሳደርነት ሾመ።ድርጅቱን ለማስተዋወቅ ብሎም የመወከል አቅም አላት ብሎ ያመነባትን አርቲስት ራሄል እንግዳን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/M1FPmHW9Wav5oGzYt5gTfuWngUnBSTVK18iFSwfjd6JbMdel2ETvAGoOSdmbCd3XvGXxZPYfvDKvwXcDYZiUF0CPfoEdKb0fJn8hJ0_6qR95JHiKQEMDJgB5Z172IIoU3VIIn-4YP-NNhFUwjqOT0mq7jUKBwuwLKzM8hz7ECiSbpC6kYEMQVv9PjUFEkj9aSQ_AoVWzufCe6jUx1zf5NMDCLmoPV0dbKO5zNHP6ZJ9j7AV0yV149DlDfENduU4E8InNBG45WE4gGvJ-NC2RfEDnSJcgRSKxdCx4MuM-RFA0pbaB26nWTE6F5eG0v8ubnQU1kW35t6xIhxHgWOJOEg.jpg

እናት ወተት እና የወተት ተዋፅኦ ማቀነባበሪያ አርቲስት ራሄል እንግዳን በብራንድ አምባሳደርነት ሾመ።

ድርጅቱን ለማስተዋወቅ ብሎም የመወከል አቅም አላት ብሎ ያመነባትን አርቲስት ራሄል እንግዳን በዛሬው እለት በብራንድ አምባሳደርነት ሾሟል።

የብራንድ አምባሳደርነቱ ዉልም ለ አንድ አመት የሚቆይ እና በ2 ሚሊዮን ብር ስምምነት የተፈረመ መሆኑ ተገልጿል ።

አርቲስት ራሄል እንግዳ  በተለያዮ የጥበብ ስራዎቿ የምትታወቅ ሲሆን ለአብነትም አደይ ተከታታይ ድራማ ይጠቀስበታል።

ርሆቦት ሀላፊቱ የተወሰነ የግል ማህበር እናት ወተት ተዋፅዖ ማቀነባበሪያ በሚል መለያ ስም  (ብራንድ) የሚታወቀው እናት እርጎ ፣የገበታ ቅቤ እና ፓስተራይዝድ ወተት በማምረት እና በማከፈፈል ላይ የሚገኝ ድርችት መሆኑን አስታውቀዋል ።

አሁን ደግሞ የምርቱን ተወዳጅነት እና የደንበኞችን ፍላጎት በማገናዘብ እርጎዎችን በኢንጆሪ ጣእም እና በማንጎ ጣእም በተጨማሪም አይስ ክሬሞችን ለማምረት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ተነግሯል ።

እናት ወተት 463 ለሚሆኑ የማህበረሰባችን ክፍል የስራ እድል መፍጠር እንደቻለም ተናግረዋል ።

ሐመረ ፍሬው

Source: Link to the Post

Leave a Reply