እናት ፓርቲ፣ መንግሥት በአዲስ አበባ በጀመረው ሠፈሮችን የማፍረስ እንቅስቃሴ “ታሪክና ሃብት የማጥፋት ዘመቻውን ባስቸኳይ እንዲያቆም” እና የቅርስ ባለሥልጣንና ቱሪዝም ሚንሰቴርም ድርጊቱን የ…

እናት ፓርቲ፣ መንግሥት በአዲስ አበባ በጀመረው ሠፈሮችን የማፍረስ እንቅስቃሴ “ታሪክና ሃብት የማጥፋት ዘመቻውን ባስቸኳይ እንዲያቆም” እና የቅርስ ባለሥልጣንና ቱሪዝም ሚንሰቴርም ድርጊቱን የመመርመርና የማረም ሚናቸውን እንዲወጡ ጠየቀ።

ፓርቲው፣ መንግሥት በከተማዋ በተለይም በፒያሳ የሚያካሂደው የሠፈር ማፍረስ ሂደት “በግብታዊነት የቀደመውን በማጥፋት አዲስ ታሪክ የመጻፍ ሩጫ ይመስላል” በማለት ተችቷል።

ሂደቱ በዚኹ ከቀጠለ የከተማዋን መነሻ አሻራ ለማየት አስቸጋሪ ይኾናል ያለው ፓርቲው፣ መንግሥት እያፈረሰ የሚገኘው ሕዝቡ ለዘመናት የገነባውን ሥነ ልቡናዊ ትስስር ጭምር ነው ብሏል።

ቅርሶች ተጠብቀው እንዲቆዩና የአገሪቱ የቀደመ ማንነት መገለጫዎች ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባም ፓርቲው አሳስቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply