You are currently viewing እናት ፓርቲ ሕግ በብዙ ሰዎች ሞትና ንብረት ውድመት፣ በሀገር ክህደት ተግባር ተሰማርተዋል በሚል የጠረጠራቸውና በሽብርተኛነት የተፈረጀ ድርጅት መሥራችና ዘዋሪ የሆኑ አካላት ሕጋዊ ሂደቱን ባል…

እናት ፓርቲ ሕግ በብዙ ሰዎች ሞትና ንብረት ውድመት፣ በሀገር ክህደት ተግባር ተሰማርተዋል በሚል የጠረጠራቸውና በሽብርተኛነት የተፈረጀ ድርጅት መሥራችና ዘዋሪ የሆኑ አካላት ሕጋዊ ሂደቱን ባል…

እናት ፓርቲ ሕግ በብዙ ሰዎች ሞትና ንብረት ውድመት፣ በሀገር ክህደት ተግባር ተሰማርተዋል በሚል የጠረጠራቸውና በሽብርተኛነት የተፈረጀ ድርጅት መሥራችና ዘዋሪ የሆኑ አካላት ሕጋዊ ሂደቱን ባልጠበቀ መልኩ መለቀቃቸውን አወገዘ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ እናት ፓርቲ ሕግ በብዙ ሰዎች ሞትና ንብረት ውድመት፣ በሀገር ክህደት ተግባር ተሰማርተዋል በሚል የጠረጠራቸውና በሽብርተኛነት የተፈረጀ ድርጅት መሥራችና ዘዋሪ የሆኑ አካላትን ሕጋዊ ሂደቱን ባልጠበቀ መልኩ ክስ በማቋረጥ መለቀቃቸውን አውግዟል። “ሁሉ በሕግ እና በሕግ ብቻ ይሁን!” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫው እንዳለው መንግስት ከሰሞኑ ምህረት በሚል በሀገር ክህደት ወንጀል የተጠረጠሩ የሽብር ድርጅት መስራቾችን መልቀቁን በግልጽ ተቃውሟል። እናት ፓርቲ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ውጥንቅጡ የወጣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዞ ወጥታ፣ ችግሯ በዘላቂነት ተፈቶ፣ ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር እንድትሆን ጽኑ ፍላጎት እንዳለው ያስታወቀው ፓርቲው ነገር ግን ሕጋዊ ሂደትን ባልጠበቀና በማናለብኝነት ውሳኔዎችን መወሰንና ተግባራዊ ማድረግ የገዥው ፓርቲ አሠራር ሆኖ ቆይቷል፤ አሁንም እየሆነ ነው ብሎታል። የትኛውም አካል የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ሰው ከሕግ በታች መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ሆኖ ሳለ በወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብም ይሁን ድርጅት በሕግ ጥላ ሥር አውሎ የመመርመር፣ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጦ የማሰናበትም ሆነ ጥፋተኛ መሆናቸውን ለይቶ ተገቢውን የእርምት እርምጃ የመውሰድ ሓላፊነት የሕግ ሥርዓቱ ተግባር ስለመሆኑም ጠቅሷል። ይሁን እንጅ ሕግ በብዙ ሰዎች ሞትና ንብረት ውድመት ጠርጥሬያቸዋለሁ ብሎ በቁጥጥር ሥር ያዋለቸውን ግለሰቦች ጨምሮ በሀገር ክህደት ተግባር ተሳትፈዋል አልፎም በሽብርተኛነት የተፈረጀ ድርጅት መሥራችና ዘዋሪዎችን ሕጋዊ ሂደትን ባልጠበቀ ሁኔታ “ክስ ማቋረጥ” ማሰናበት በሕግ ተቋማት ሥራ ላይ ያለውን ጣልቃገብነት ከማሳየቱም ባሻገር የፈላጭ ቆራጭነት ማሳያ ነው ሲል አውግዟል። በሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በሰላማዊ ዜጎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ፣ የአካል ጉዳት ያደረሱ፣ ንብረት ያወደሙ ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ እና አፋር ሕዝቦችን ያፈናቀሉ እና ለትግራይ ሕዝብ ለአሥርት ዓመታት በሰቆቃ ሕይወት መኖር ተጠያቂ የሆኑ፣ እናቶችና ሕጻናት እንዲደፈሩ ያደረጉ አመራሮችን መለቀቅ ተቃውሟል። በሕግ ጥላ ሥር ለማዋል የሀገር አለኝታ በሆኑ የቁርጥ ቀን ልጆች የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ከቁስላቸው ሳያገግሙ፣ ቁጣቸው ሳይበርድ፣ ከሀዘናቸው ሳይጽናኑ ኢሕጋዊ በሆነ ሁኔታ ታሕሳሥ 29 ቀን 2014 ዓ.ም የተወሰነው ውሳኔ የፓርቲውን አምባገነንነት የሚያሳይ ነው ብሎታል። የመንግስት ውሳኔ ለስልጣኑ ማስጠበቂያ እንጂ ለሀገር ሉዓላዊነትና ለሕዝብ ደህንነት ስሜት የማይሰጠው የመሆኑ ማሳያ እንደሆነም ጠቁሟል። ከብዙ ታሳሪዎች መካከል “በእድሜ የገፉ ስለሆነ” በሚል ማታለያ እና ውሀ በማይቋጥር ምክንያት ሀገር ለሕልውና እያደረገች ያለውን ጦርነት ዓላማ የሳተ፣ የሕግ አሠራር ሂደትን የጣሰ፣ በግለሰቦችና ገዢው ፓርቲ ፍላጎት ብቻ ዜጎች የሚታሠሩበትና የሚፈቱበት ያሳያል ነው ያለው እናት ፓርቲ በመግለጫው። ስለሆነም ለፖለቲካ ትርፍ እና ለስልጣን ማስጠበቂያ ሲባል የሕግ አሠራርን ወደጎን በመተው በስሜትና በማንአለብኝነት የሚወሰኑ ውሳኔዎች ሀገራችንን አሁን ካለችበት ሁኔታ ወደከፋ አዘቅት ይዟት እንዳይጓዝ ፓርቲው ሥጋት እንዳለው ገልጧል፡፡ በመጨረሻም እርቅና ሰላምን ከማምጣት አኳያ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀው ቢሆንም እንዲህ ያሉ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶች የሚኖሩ ከሆነ ውጤቱ ከነበረው የተለየ እንደማይሆን አንድ ምልክት ተደረጎ ሊወሰድ ይገባል፤ አስፈጻሚው አካልም በሕግ የተገደበ ሥልጣኑን ብቻ እንዲወጣ እናሳስባለን ሲል መግለጫውን ቋጭቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply