You are currently viewing እናት ፓርቲ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና በተባለ ቀበሌ በንጹሓን ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ በጽኑ አወገዘ፤ ድርጊቱ የሕወሓት የጭካኔ ጥግ ማሳያ ነው ሲል ገልጾታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

እናት ፓርቲ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና በተባለ ቀበሌ በንጹሓን ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ በጽኑ አወገዘ፤ ድርጊቱ የሕወሓት የጭካኔ ጥግ ማሳያ ነው ሲል ገልጾታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

እናት ፓርቲ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና በተባለ ቀበሌ በንጹሓን ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ በጽኑ አወገዘ፤ ድርጊቱ የሕወሓት የጭካኔ ጥግ ማሳያ ነው ሲል ገልጾታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ እናት ፓርቲ በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ወረዳ፣ ጭና ቀበሌ በንጸሓን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በጽኑ እንደሚያወግዘው አስታውቋል። እናት ፓርቲ በመግለጫው የጦር ቀጠና ሆና በቆዬችው ጭና ቀበሌ የሞተውን የሚቀብሩ፣ የቆሰለውን የሚጠግኑ፣ የጠማውን የሚያጠጡ፣ ሀገር በሰላም ውላ እንድታድር የሚጸልዩ ካህናት፣ እናትና አባቶች እንደቅጠል መርገፋቸውን አመላክቷል። ከምኔው የመሣሪያ ድምጽ በራቀልን እያሉ ጆሯቸውን ጠቅጥቀው የሚውሉ ሕጻናት ጣረ ሞት ቤታቸው ድረስ መጥቶ በነብስ ወከፍ መሣሪያ ጭምር ተጨፍጭፈዋል ያለው እናት ፓርቲ ይህ ጨካኝ የትሕነግ ቡድን በዜጎቻችን ላይ ያደረሰው ግፍ አልበቃውም ሲል ገልጾታል። “በጋጣው ያሉ እንስሳትንም አልማሯቸውም፣ ውሾችም ላይ ሳይቀር ተኮሱ፣ ሁሉም በየፊናው ወደቀ፤ በጭና ምድር የደም ጎርፍ ይወርድ ጀመር፡፡” ሲል የወራሪውንና አሸባሪውን አውሬያዊ ድርጊት በመግለጫው አስፍሯል። ከአንድ መቶ ሃያ በላይ ንጹሓን በዚያች ጀንበር ቤት ለቤትና በየዋሻው የፈጀው ከሰውነት ይልቅ ለጭራቅነት የቀረበው የሕወሃት ቡድን አላማው አካባቢውን ምድረ በዳ ማድረግ እንደነበር ግልጽ አድርጓል ነው ያለው እናት ፓርቲ በመግለጫው። ኦነግ ሸኔ በምሥራቅ ወለጋ- ኪረሞ፣ ሕወሓት በሰሜን ጎንደር- ጭና ያልተቀደሰ የጋብቻ ፊርማቸውን በንጹሓን ደም ማፅደቃቸውን የገለፀው ፓርቲው ይሄ እኩይ ቡድን እያረጀ፣ እየሰከነ፣ እየተማረ ሳይሆን ይበልጥ የክፋት ዝናር የሚታጠቅ፣ በኮሚኒስቶች ጋን ተጠምቆ የጠጣው የወይን ስካር ያለቀቀው መሆኑን ደጋግሞ ለዓለም አሳይቷል ብሏል። እናት ፓርቲ በንጹሓኑ ፍጅት የተሰማውን ሐዘን እየገለጠ ለሟቾች እረፍተ ነፍስን፣ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል። እንዲህ ያሉ ተግባሮች ሕወሓት በተቆጣጠራቸው የሰሜን ወሎ አካባቢዎች ዳግም ላለመፈጸማቸው ዋስትና የለምና መንግስት አስፈላጊውን ርብርብ ሁሉ አድርጎ እንዲታደጋቸውም አሳስቧል። መገናኛ ብዙኃን፣ በቅንነት የምትተጉ የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ሲቪክ ተቋማት እንዲህ ያለው እኩይ ድርጊት በጦር ወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ በማጋለጡ ሂደት እንድትረባረቡ እንጠይቃለን ብሏል፡፡ በመጨረሻም እንዲህ ያለውን የፈሪዎች በትር በንጹሓን ላይ የምታሳርፉ እኩያን ስለነገ የልጆቻችሁ ዓለም ብላችሁ ከንጹሓን ዜጎች ጭፍጨፋ እንድትቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን ብሏል እናት ፓርቲ ለአሚማ በላከው መግለጫ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply