እናት ፓርቲ ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል የገቡትን ጨምሮ የመዋቅራዊ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል ያላቸው ተፈናቃዮችን ህዝቡ እንዲታደጋቸው ጥሪ አቀረበፓርቲው በላከልን መግለጫ ላይ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/NZdkzTGylCO4wwZ-u2yfIPUAw_uu4pBJsMQ753lo3tEbMOKD9O85E7W9hU14_dnprSVBAaX9uRK39ZfHNv3v1SzXlotAOha742ml2sEFX2BHNFRmmnBJ8G2-TcpaIKgvTkqsjczSALD3BH53o7hEVW_X5mMrbcRznkluw3bhXBIlwPh5WCkkf_YPiznByJ8mIq2GWvZwnewL3QeehpFVHihs4KQh7HGlhPHagZ7Hd_QrwGwypV63jKBOkQzzBftqJ3Kx5bFsT7e6ViU0iGDxEqCID-jCkEOfCijxSqklzfYfBLdB_pArBW6_gmyKnqTUPNA7GWeRCn-v8xB0f4-N8w.jpg

እናት ፓርቲ ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል የገቡትን ጨምሮ የመዋቅራዊ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል ያላቸው ተፈናቃዮችን ህዝቡ እንዲታደጋቸው ጥሪ አቀረበ

ፓርቲው በላከልን መግለጫ ላይ እንዳሰፈረው” የመዋቅራዊ ጥቃትና ጦርነቱ ሰላባ የሆኑ” ያላቸው ”ተፈናቃይ ወገኖች ህዝቡ በአፋጣኝ ይድረስላቸው”ሲል ጠይቋል፡፡

ፓርቲው”በሀገራችን ሞትን እየተለማመድን፣ የሞተው ሰው ቁጥርና የአሟሟቱ የዘግናኝነት መጠን ያነጋግር ካልሆነ እንጂ የጅምላ ፍጅትና ዕልቂት የሚስገርም አልሆነም፡፡” ሲል ወቅሷል፡፡

ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የተከሰቱትን ዘግናኝ ወንጀሎችን በመግለጫው ያስታወሰው ፓርቲው ድርጊቶቹ”ዝም በመባላቸው ዛሬ ሰው ከነህይወቱ እያገላበጥን መጥበስ ላይ ተደርሷል” ሲል ኮንኗል፡፡ አክሎም ”ይህም ዝም ስለሚባል ነገ ምን እንደሚደረግ መገመት አያዳግትም፡፡” ብሏል፡፡

ፓርቲው በመግለጫው”በቅርቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ መድረሻ ያጡ ምስኪን ኢትዮጵያን አንገት ማስገቢያ ጎጆ አጥተው እንደ ኳስ ከቦታ ቦታ ሲላጉ እያየን ሃይ ባይ ስላጣን መቶሺዎች በመዋቅራዊ ጥቃት ሰበብ አማራ ክልል፣ ፍኖተ ሰላም አካባቢውን አጥልቅቀዋል፡፡” ሲል አመለክቷል፡፡

እናት ፓርቲ ” ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ሁኔታ” በህወሓት በፓርቲው አገላለፅ ትህነግ፣ አማካይነት ወደምድራዊ ሲዖል በመቀየሩ፣ ማህበረሰቡ እግሩ ወዳደረሰው በገፍ በመሰደድ በመጀመሩ አንዱ መዳረሻ ወደሆነው ቆቦና ሰቆጣ ሆኗል ሲል ገልፆል፡፡

ስለዚህም በመቶሺዎች የሚቆጠሩ በአማራ አፋር ክልል፣ አንዲሁም ከትግራይ ክልል እየገቡ ላሉት ” ተፈናቃዮች ” የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲድረስላቸውና እንዲታደጋቸው በመግለጫው ጠይቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply