እናት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሩ በፖሊስ እንደታሰሩበት አስታወቀ

ሐሙስ መስከረም 26 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የእናት ፓርቲ የላዕላይ ምክር ቤት አባል እና የመተከል ምርጫ ክልል 1 የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ የሆኑት ሀብታሙ ይታየው መስከረም 23/2015 ጠዋት “እንፈልግሃለን” ተብለው በፖሊሶች ከቤታቸው መወሰዳቸውን ፓርቲው አስታወቀ።

ሀብታሙ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት እንደሚገኙ የገለጸው ፓርቲው፤ እስከአሁን ድረስ የተከሱበትን ምክንያት እንዳላወቁና ፍርድ ቤትም እንዳልቀረቡ ተናግሯል።

እናት ፓርቲ የምርጫ ተወዳዳሪ ዕጩ ያለመከሰስ መብት በአዋጅ የተሰጠ መብት መሆኑ እየታወቀ አዋጁን በመጣስ በአመራሩ ላይ የተፈጸመው እስር እንዳሳሰበው ገልጿል።

አመራሩ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ለሚመለከታቸው አካላት ማለትም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በደብዳቤ ማሳወቁን የገለጸው ፓርቲው፤ ጉዳዩንም በቅርበት እየተከታተለው እንደሚገኝም አስታውቋል።

The post እናት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሩ በፖሊስ እንደታሰሩበት አስታወቀ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply