
#እናት_ፓርቲ_ውጭ_ካሉ_ኢትዮጵያውያን_ጋር_ምክክር_አደረገ! መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እናት ፓርቲ መጋቢት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ውጭ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ፣ በእናት ፓርቲ አጠቃላይ እንቅስቃሴና፣ መወሰድ ስለሚገባው ድርሻ ዙሪያ ምክክር አድርጓል። በበይነ መረብ (Zoom) አማካኝነት የተደረገው ምክክር በአጠቃላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አፍሪካ ተሳትፈዋል። በዕለቱም ተጋባዥ አርቲስቶች ተገኝተው ማነቃቂያ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ኹሉም ተሳታፊዎች ከዚህ በኋላ ፓርቲው በሚያደርገው እንቅስቃሴ ኹሉ ከጎኑ እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል። ፓርቲው እንዲህ ያለውን ተግባር እንደሚቀጥልበት ያስታወቁት የፓርቲው የውጭ ግንኙነት ሓላፊ ዶ/ር ዓለማየሁ ቀጣይ ውይይቶችና የፓርቲውን የውጭ ቻፕተሮች የማስፋፋት ሥራ በፍጥነት ይጀመራል ብለዋል። ውድ ጊዜያቸውን አጣበው ለተገኙ ተሳታፊዎች ምሥጋና ያቀረቡት የፓርቲው ተ/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰይፈሥላሴ አያሌው “ሀገር ከገባችበት ምጥ የምንችለውን በማድረግ ለማገላገል ጥረታችን ይቀጥላል፤ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ከጎናችን ይቁም፤ እኛም በአደራችን እንደምንገኝ ቃል እንገባላችኋለን” ብለዋል። እናት ፓርቲ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ ላይ በቀጣይም ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር እንደሚመክር በመድረኩ ተገልጿል። ፈጣሪ ሀገራችን ኢትይዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ እናት ፓርቲ መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓ. ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post