You are currently viewing እኔን ከነካሀኝ የምክር ቤት አባልም ብትሆን አስቀፈድድሃለሁ/ መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ይነበብ#ሼር ይደረግ! ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ የአማራ “አንቂ” ነን የሚሉት ሁሉ አንድ…

እኔን ከነካሀኝ የምክር ቤት አባልም ብትሆን አስቀፈድድሃለሁ/ መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ይነበብ#ሼር ይደረግ! ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ የአማራ “አንቂ” ነን የሚሉት ሁሉ አንድ…

እኔን ከነካሀኝ የምክር ቤት አባልም ብትሆን አስቀፈድድሃለሁ/ መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ይነበብ#ሼር ይደረግ! ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ የአማራ “አንቂ” ነን የሚሉት ሁሉ አንድ ከስማቸው መረዳት እንደሚቻለው በነገድ ኦሮሞ የሆኑ ግለሰብ “..ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ፤የፍትህ ስርዓቱ ስራውን ጀመረ” ወዘተ የሚሉ ቧልቶችን እየነገሩን ነው። ከጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብት መነሳት በስተጀርባ ያለውን ሴራ ግን ሊነግሩን አልፈለጉም(ከድንቁርና የመነጨ) ሊሆን ይችላል።የዚህ ሰውዬ ያለመከሰስ መብት ተነሳ የተባለው”የሙስና ወንጀል” ፈፅሞ ነው።(ከጠቅላይ ሚንስትሩ በላይ ሙሰኛ ባይኖርም)ጉዳዮ በፓርላማ የህዝብ እንደራሴ ነኝ ብለህ ጥፍር ማውጣት ከጀመርክ አባል ብትሆንም ከእግር እስከ ራሱ በተቆጣጠርኩት የፍትህ ስርዓት ሰበብ “ሙሰኛ” እያልኩ አስቀፈድድሃለሁ፤ዋ! የሚል መልዕክት ያለው ነው። በራሱ ነገድ አባላት ላይ “ሀ”ብሎ የጀመረውም ለሴራው ነው።”እንዴት የእኛ ብሔር ይታሰራል”? ለሚለው ቀጠይ ጥያቄ ባላንስ መሆኑ ነው።በስተመጨረሻም ትንሽ ውኒጥ ውኒጥ የሚሉ ብአዴን አባላትን፣ እንኳን እናንተን ባሮቼን ይቅርና የህዝብ እንደራሴ አስሬአለሁ፤ስለዚህ አርፋችሁ ተቀመጡ የሚል ጠንከር ያለ የተግባር ማስፈራሪያ መሆኑ ነው። እና ጮቤ ላይ ያላችሁ እንከፎች በተከፈተላችሁ ቦይ አትፍሰሱ :: “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply