ደብረ ብርሃን: መጋቢት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ እና መርሀቤቴ ወረዳዎችን የሚያገናኘው የጀማ ድልድይ ዛሬ በመሰበሩ መንገዱ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኗል። ይህ መንገድ ከአዲስ አበባ በሚዳ መርሀቤቴ በኩል እስከ ደሴ ድረስ የሚወስድ በአስፋልት ግንባታ ላይ የሚገኝ መንገድ ነው። ከደብረ ብርሃን ወደ መርሀቤቴ ሚዳና ወረኢሉ ለመጓዝም የሚያገለግለው መንገድም ይህ መስመር ነው። ዛሬ የመሰበር አደጋ የደረሰበት […]
Source: Link to the Post