የስራና ክሆሎት ሚኒስቴር ከፍሎለስ ኤቨንትስ ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁት እንቆጳ ሰሚት ትኩረቱን በሥራ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ላይ በማድረግ ከጥቅምት 1 – 2 /2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።
ዛሬ በተጀመረዉ ጉባኤ ላይ ሥራ ፈጣሪዎች፣ ቴክኖሎጂ አልሚዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ጀማሪ የንግድ ሥራ ባለሙያዎች፣ ኢንቨስተሮች እንዲሁም የትምህርትና የፋይናንስ ተቋማት ተሳታፊ ሆነዋል።
ጉባኤው ኢትዮጵያ በዲጂታል የሥራ ፈጠራ ያላትን እምቅ አቅም በማስተዋወቅ በዘርፉ የሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎችን ማስፋት ነዉ የተባለ ሲሆን በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡
“የአፍሪካም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር እየጨመረ መምጣት እንደ ችግር መታየት የለበትም” ያሉት አቶ ንጉሱ ጥላሁን በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ “ይህንን የህዝብ ቁጥር መጨመር ወደ ዕድል በመቀየር ለስራ ዕድል ፈጠራ መጠቀም ይቻላል” ብለዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ በርካታ ሀገር ኢንቨሰተሮች እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ከማላዊ፣ቦትስዋና፣ጃፓን፣አሜሪካ እና ህንድን የመሳሰሉ ከ26 በላይ ሀገር ዜጎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልፃል።
በርካታ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ኢንቨስተሮች በተለይም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ እና ስራ ፈጣሪዎች ሀሳብ ያለቸዉና ሀሳባቸዉን ወደ ተግባር የቀየሩ ድርጅቶች እንደሚሳተፉም አቶ ንጉሱ አስታዉቀዋል።
ከውይይቶቹ ጎን ለጎንም ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት እና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት ኤግዚቢሽን በመካሄድ ላይ ይገኛል።
እንቆጳ የሚለዉ ቃል በግዕዝ የወርቅ ጥሬ ሀብት ማለት ነዉ፣ ስለዚህም ያለንን ሀብት ለዓለም ማሳየት አለብን በተለይም በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ላይ ተብሏል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ጥቅምት 01 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post