እንባ ጠባቂ ተቋም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ26,900 በላይ ቅሬታዎችን ከሕዝብ መቀበሉን አስታውቋል። ተቋሙ፣ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 26 ሺህ 912 ሰዎች የአስተዳደር በደል እንደተፈጸመባቸው በ…

እንባ ጠባቂ ተቋም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ26,900 በላይ ቅሬታዎችን ከሕዝብ መቀበሉን አስታውቋል።

ተቋሙ፣ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 26 ሺህ 912 ሰዎች የአስተዳደር በደል እንደተፈጸመባቸው በመግለጽ አቤቱታ ማቅረባቸውን ጠቅሷል።

በዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመቀበል አቅዶ የነበረው 2 ሺህ 823 የአቤቱታ መዝገቦችን እንደነበር የገለጠው ተቋሙ፣ የነጻ ጥሪ መቀበያ የስልክ መስመሩ ከተቋሙ አቅም በላይ በኾነ ምክንያት ለሰባት ወራት አገልግሎት ባለመስጠቱና ባንዳንድ ክልሎች ባሉ የጸጥታ ችግሮች ሳቢያ 1 ሺህ 454 የአቤቱታ መዝገቦችን ብቻ እንደተቀበለ ገልጧል።

በተያያዘ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለእንባ ጠባቂ ተቋም ምክትል ኮሚሽነሮችን ለመሾም የእጩዎች ጥቆማዎችን መቀበሉን ከቀናት በፊት መግለጡ አይዘነጋም።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply