እንካችሁ ጀግና ዳግማዊ ደጃዝማች አበረ ይማም ኮማንዶ (ሳጅን መልካሙ ሰማኸኝ)!!             አሻራ ሚዲያ       ታህሳስ 3/2013 ዓ•ም ባህርዳር…

እንካችሁ ጀግና ዳግማዊ ደጃዝማች አበረ ይማም ኮማንዶ (ሳጅን መልካሙ ሰማኸኝ)!! አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 3/2013 ዓ•ም ባህርዳር…

እንካችሁ ጀግና ዳግማዊ ደጃዝማች አበረ ይማም ኮማንዶ (ሳጅን መልካሙ ሰማኸኝ)!! አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 3/2013 ዓ•ም ባህርዳር ደጃዝማች አበረ ይማም ጣሊያን ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት በሞከረችበት ጊዜ የጎጃምን አርበኞች አስተባብረው ሲዋጉ በጣሊያን ጦር ደረታቸው ላይ ተመተው ጉዳት ደርሶባቸው ነበር። ታድያ ሽንፈትን የማይወዱት ደጃዝማች አበረም ወዲያው አገግመው ዳግም ወደ ጦርነቱ ተመልሰው ነበር ከጠላት የተናነቁት። ታሪክ ራሱን ይደግም ዘንድ እነ ደጃዝማች አበረ ይማም፣ የነኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ፣ እና የዘመኑ የአማራ ህዝብ አለኝታ ከሆኑት ታጋይ ዘመነ ካሴ፣ ዶ/ደሳለኝ ጫኔ፣ እና በርካታ የአገር እና የህዝብ መከታ የሆኑ ጀግኖችን ካፈራችው የጀግኖች አምባ አቦካቦክ ሜጫ ስለተገኘው ኮማንዶ መልካሙ ሰማኸኝ ገድል በአጭሩ እንደሚከተለው ቀርቧል። መልካሙ ሰማኸኝ ተወልዶ ያደገው በም/ጎጃሟ መራዊ ከተማ ሲሆን አስተዳደጉም ልክ እንዳባቶቹ ባልሸነፍም ባይነት በተሰለፈበት ሁሉ ቀዳሚ እንደሆነ የቅርብ ጓደኞቹ መስክረውለታል። ታድያ ይህ መልከ መልካም ኮስታራ ጀግና ከብዙ ገድሎቹ መካከል የአማራ ልዩ ኃይልን ከተቀላቀለ ጀምሮ ከጓዶቹ ጋር በመሆን የፈፀመውን ጀብዱ ወደናንተ እናቀርባለን። በ2010 ዓ•ም ነበር የአማራ ልዩ ኃይልን እንደ አዲስ ለማደራጀት በጀነራል አሳምነው ፅጌ ጥሪ ተደርጎለት ያለውን ወታደራዊ አቅም ለሌሎች የአማራ ልዩ ሀይል ለማስተላለፍ በአሰልጣኝነት የተቀላቀለው። የመጀመሪያውን ዙር የአማራ ልዩ ሀይል ኮማንዶ ጨምሮ ሁለት (2)ዙር ብቁ ኮማንዶዎችን አሰልጥኗል። ከዛም እሱን ጨምሮ ሰማኒያ(80) አባላትን የያዘውን #ልዩ ሻለቃ ኮማንዶ ሁለተኛ ብርጌድን ተቀላቀለ። ከዛም የህወሓት ከሀዲው ቡድን በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ በተደረገው ህግን የማስከበር እርምጃ ሙሉ የብርጌዱ አባላትን ጨምሮ በራያ ግምባር እንዲሰለፍ ተደረገ። ከመከላከያ ሰራዊት ፣ከአማራ ሚሊሻ እና ፋኖ ጋር የህውሓትን ጦር ለመደምሰስ የተሰለፈው የልዩ ሻለቃ ኮማንዶ ሁለተኛ ብርጌድ አባል የሆነው ሳጅን መልካሙ ሰማኸኝ የመከላከያን የከባድ መሳሪያ ሽፋን በመጠቀም ጠላትን ያርበደብደው ጀመር። የራያ ሜዳማ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ሁለት ቀን እንኳን ያልወሰደበት የአማራ ልዩሀይል መከላከያ ሰራዊታችን ካቅሜ በላይ ነው ያለውንና ህወሓት አለኝ የምትለው የግራካሶ ትልቁን ምሽግ ለመቆጣጠር ትንቅንቁ ጀመረ። የመከላከያ ሰራዊት እግረኛ ሰራዊት የግራካሶን ተራራማ ቦታዎች ለቆ እንዲወጣ እና ባለእርግቦቹ የአማራ ልዩሀይል ኮማንዶዎች እና የመከላከያ የከባድ መሳሪያ ሽፋን ተኩስ ተኳሾች ብቻ ቀሩ። ውጊያውም ከጠዋት ጀምሮ ያለማቋረጥ ለስምንት (8) ሰዓት ያክል ተደረገ። ድልን እንጂ ሽንፈት የማያውቀው የአማራ ልዩ ኃይል መጠነኛ እረፍት ካደረገ በኋላ ምሽቱን ተራራ እየቧጠጠ አንድ መግቢያ እና መውጫ ያለውን ቀለበታማ ምሽግ ለማስለቀቅ እልህ አስጨራሽ ውጊያ አደረጉ ይሄኔ ለብርጌዷ የቀኝ እጅ የሆነው ክንደ ነበልባል ሳጅን መልካሙ ሰማኸኝ ታፋው ላይ ተመቶ ወደቀ ። በውጊያ ላይ አይደለም መቁሰል መሰዋት እንዳለ የተረዱ ጓዶቹ ሳጅን መልካሙን ወደ ህክምና ከወሰዱት ውጭ ሌሎች ውጊያውን ቀጠሉ። መልካሙም መካከለኛ ህክምና እየተደረገለት እያለ የህወሓቱ ከሀዲ ቡድን በድል አድራጊነት ዳንኪራ ሲረግጥ ታየው ከህመሙ እንዲያገግም ላዩ ላይ የተጠቀለለውን ፋሻ አሽቀንጥሮ እያነከሰ ጉዞውን ጥሏቸው ወደ መጣው ጓዶቹ አደረገ ጓዶቹም የመልካሙን ተመልሶ መምጣት በአዲስ መንፈስ የህወሓትን ከሀዲ ቡድን አመሰቃቀሉት። የአማራ ልዩ ኃይልን ዩኒፎርም ሲያይ ግራና ቀኙ የሚጠፋበት የህወሓት ቡድን ብርክ ይይዘው ጀመር። ግፈኞችን የማይታገሰው ባለ እርግቡ የአማራ ልዩ ኃይልን ከነ ቁስሉ ዳግም የተቀላቀለው ሳጅን መልካሙ ሰንሰለታማውን የግራካሶ ምሽግ ከነ ጓደኞቹ ደርምሶ ገባ።ከሞርታር እስከ ድሽቃ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀው የህወሓት ከሀዲ ቡድን የነፍስወከፍ ክላሽ በታጠቀው የአማራ ልዩሀይል ተደመሰሰ።ሳጅን መልካሙም ከልዩ ሻለቃ ሁለተኛ ብርጌድ አባላት ጋር በመሆን የደጃዝማች አበረ ይማምን ታሪክ ደገመ። ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !!

Source: Link to the Post

Leave a Reply