እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…     ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ…

እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ…

እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ለብርሀነ ጥምቀቱ ያስተላለፈው መልዕክት:_ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለንቅናቄያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን ለ2013 ዓ.ም የከተራ እና የጌታችንና የመድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በመላ አገራችን በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በአደባባይ ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል ከዋዜማው ከከተራ ጀምሮ ለየት ባለና ባሕላዊና ኃይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ይከበራል። ጥምቀት በዓለም የሳይንስ፣ የባሕልና የትምህርት ጥናት ማዕከል(UNESCO) በማይዳሰስ ቅርስነት በመመዝገቡ በዓሉን ለመታደም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በርካታ ቱሪስቶች ስለሚመጡ በዓሉን ስናከብር እሴቶቻችንንም ለሌላው ዓለም የምናስተዋውቅበት በመሆኑ ለአካባቢያችን ሰላም ዘብ በመሆን፣ ከኮሮና ወረርሽኝ በመጠበቅ ሊሆን ይገባል። በተጨማሪም በዓሉን ስናከብር የሕዝባችንን ነባር የመተሳሰብና የመረዳዳት ባሕልን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ከተቸገሩ እንዲሁም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በማንነታቸው ምክንያት በግፍ ተፈናቅለው በመጠልያ ካምፖች የሚገኙ ወገኖቻችንን በመደገፍ እንዲሆን አብን ጥሪውን ያቀርባል። በድጋሜ መልካም በዓል ! የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)!

Source: Link to the Post

Leave a Reply