
እንኳን ለ83ኛው የአገው ፈረሰኞች ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 23 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ 83ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል “አምራች ፤ዘማች የአገው ፈረሰኞች ማህበር “በሚል መሪ ቃል በእንጅባራ ከተማ እየተካሄደ ነው። ይህ የአገው ፈረሰኞች በዓል በርካታ ታዋቂ የክብር እንግዶች በእንጅባራ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በባህላዊ አልባሳት እና በፈረሰኞች ልዩ የአለባበስ እና የግልቢያ ጥበብ አምሮ በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል። ዓመታዊ ክብረ በዓሉ በድምቀት እንዲከናወንም የአገው ፈረሰኞች ማህበር ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው። ይህ የሚያምረው የአገው ፈረሰኞች ልዩ በዓል በዩኔስኮ ይመዘገብ ዘንድ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል። እንኳን ለአገው ፈረሰኞች በዓል አደረሳችሁ! ፎቶ_አዊ ኮሚዩኒኬሽን
Source: Link to the Post