You are currently viewing እንደሚታወቀዉ ጦርነት በጎ ጎን አለዉ ለማለት ደስ ባያሰኝም ለኛ ሀገር ለስነ ግጥም አስተዋፅኦ አለዉ።  ግርማቸው ሲሳይ እስኪ የምናዉቀዉን እናዋጣ ምኒልክ ባይፈጠር እጣ ፈንታችን ምን ሊሆን…

እንደሚታወቀዉ ጦርነት በጎ ጎን አለዉ ለማለት ደስ ባያሰኝም ለኛ ሀገር ለስነ ግጥም አስተዋፅኦ አለዉ። ግርማቸው ሲሳይ እስኪ የምናዉቀዉን እናዋጣ ምኒልክ ባይፈጠር እጣ ፈንታችን ምን ሊሆን…

እንደሚታወቀዉ ጦርነት በጎ ጎን አለዉ ለማለት ደስ ባያሰኝም ለኛ ሀገር ለስነ ግጥም አስተዋፅኦ አለዉ። ግርማቸው ሲሳይ እስኪ የምናዉቀዉን እናዋጣ ምኒልክ ባይፈጠር እጣ ፈንታችን ምን ሊሆን ይችል እንደነበር ለማስገንዘብ የፈለገ ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ በማለትይገልፃል በምኒልክ ቤት ዉስጥ እንዳደገ ለሚነገርለት ለጀግናዉ የጦር መሪ ለፍታዉራሪ ገበየሁ እንዲህ ሲሉ ተቀኙ የአድዋን ስላሴ ጠላት አረከሰዉ ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰዉ ከአድዋ ጦርነት በፊት በፍታዉራሪ ገበየሁ የሚመራዉ ጦር አምባ አላጌ ላይ የጣልያንን ጦር ደህና አድርጎ ጠልዞታል።በዚህም የጦሩን መሪ ሜጀር ቶሰሊን ጨምሮ 2000 የጣልያን ጦር ሙቷል።እንግዲህ ይህ ጀግናችን ባድዋዉ ጦርነት የጣነዉ ነዉ። ባገራችን ጀግኖች ቢሞቱም በሌሎች የምር ጀግኖች እንደሚተኩ ለመግለፅ የፈለጉ ደግሞ ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ በማለት ተቀኝተዋል። ደጃች ባልቻ ባድዋዉ ጦርነት ጀግንነቱን ያስመሰከረ እና ከ 40 አመት በሗላም ጣልያንን በመዋጋት ለሀገሩ መስዋእት ሁኗል። ሌላዉ በአድዋ ጦርነት አነጣጥሮ ተኳሽነቱን የጥልያንን መድፍ ባፉ በማጉረስ ላስመሰከረዉ ለሊቀመኳስ አባተ ቦያሌዉ እንዲህ ሲሉ ተቀኙ አባተ አባ ይትረፍ ነገረኛ ነዉ ይህን መድፍ ከዚያ መድፍ አቆራረጠዉ አበሻ ጉድ አለ፣ ጣልያን ወተወተ አይነ ጥሩ ተኳሽ ቧ ያለዉ አባተ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply