You are currently viewing “እንደ ሀገርም ሆነ በውጭ ሀገር ዋግ መልሶ እንዲቋቋም በየትኛውም አግባብ ካልተሰራ ዋግ አሁንም ብዙ እርምጃዎች ወደ ኋላ ያስቀረ ሁኔታ ላይ ወድቃለች።”  ዋግኽምራ ኮሚዩኒኬሽን! አማራ ሚዲያ…

“እንደ ሀገርም ሆነ በውጭ ሀገር ዋግ መልሶ እንዲቋቋም በየትኛውም አግባብ ካልተሰራ ዋግ አሁንም ብዙ እርምጃዎች ወደ ኋላ ያስቀረ ሁኔታ ላይ ወድቃለች።” ዋግኽምራ ኮሚዩኒኬሽን! አማራ ሚዲያ…

“እንደ ሀገርም ሆነ በውጭ ሀገር ዋግ መልሶ እንዲቋቋም በየትኛውም አግባብ ካልተሰራ ዋግ አሁንም ብዙ እርምጃዎች ወደ ኋላ ያስቀረ ሁኔታ ላይ ወድቃለች።” ዋግኽምራ ኮሚዩኒኬሽን! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ዋግኽምራ ኮሚዩኒኬሽን በዋግና አካባቢው ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ የሚከተለውን መረጃ አጋርቷል:_ ከጥቅምት እስከ ጥቅምት ምድረ ዋግ እና ህዝቦቿ በቀጥተኛ እና ኢ-ቀጥተኛ ትግል ላይ እና ሰቆቃ ላይ ናቸው። በዚህ ዓመት የዋግ አርሶ አደሮች ማሳቸውን ተረጋግተው ማረሱ ይቅርና ያረሱትንም ማረም አልቻሉም። ሚያሳዝነው ግን አልፎ አልፎ የታረሱ ሰብሎችንም መሰብሰብ አለመቻላቸው ነው። ሚገርመው ደግሞ የአንበጣ መንጋም ሰብሎችን፥ የእንስሣት ግጦሽ ቦታዎችን እና እጸዋትን ወደ አፈር እየቀየራቸው እንደሆነ ከሰሃላ ሰየምት ወረዳና ከዝቋላ ወረዳ መረጃዎች ደርሰውናል። ሌሎች ወረዳዎች ላይም በተመሳስይ እንደተከሰተ መረጃዎች ያመላክታሉ። መረጃዎቹ እንደሚያሳዩት የአንበጣ መንጋው በመንግስት በተለያየ ማምከኛ ዘዴ እንዳይመክን የመንግስት አሁናዊ ሁኔታው ይታወቃል። የአከባቢው ህብረተሰብ በዘልማዳዊ ዘዴዎች የማባረሩን ስራ በተደራጀ እንዳይሰራ መላ ዋግ ህዝብ ከፊሉ በየበረኻው ተበትኖ ብዙሀኑ በየቀያቸው አስቸጋሪ ህይወት ውስጥ ያሉ መሆኑና እጅግ ውስኖች ተፈናቅለው በተለያዩ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ያሉ በመሆኑ ነገሩን ” ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሆን አድርጎታል። እጅግ አስከፊው ሁኔታ ግን ከሰሃላ ሰየምት ወረዳ ውጭ ባሉ ሰድስቱ ወረዳዎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሚገኘው መላ የዋግ ህዝብ አሁን ያለበትን ሁኔታ በህይወት ቆመህ ከምትሰማ ሞትህን ትመኛለህ። ሁኔታው እንዲህ ነው አሁን ዋግ ውስጥ:_ ጨውና በርበሬ የለም፤ ዘይት የለም፤ መድሀኒት የለም፤ በመሆኑም በደበኛ የህክምና ሰራው እንደተጠበቀ ሆኖ እንደ ደም ግፊት፣ ስኳር፣ Hiv እና መሰል ክሮኒክ የሆኑ በሽታዎች ታማሚ ታካሚዎች ህልውና አዳጋ ላይ ወድቋል፤ እየሞቱም ነው። አንዲትም እናት ጤና ጣቢያ እና ሆስፒታል ሂዳ መውለድ አትችልም፤ በመሆኑም እናቶች በወሊድ ምክንያት ለሞት እየተዳረጉ ነው። መብራት የለም፤ ነዳጅ የለም፤ ስለዚህ እህል ሚፈጭ የለም። ወይም እናቶች በእጃቸው ይፈጫሉ ማለት ነው። እሱም እህሉ ከተገኘ። ከወራጅ በስተቀር ውሀ የለም፤ የሸቀጣሸቀጥ ዓይነት ከትንሿ ክብሪት ጀምሮ ለናሙና የሚሆን የለም። ተሸምቶ የሚበላ የሰብል ዓይነት ገበያ ላይ የለም። በጥቅሉ የኑሮ ሂደትን ምትመራበት የግብይት ሂደትና የግብይት የገበያ ግብዓት የለም፤ ይህ ሁኔታ ባለበት የሰው ልጅ በህይወት ይኖራል ብለን ማሰብ እንችላለን? ፍርዱን እናንተው ስጡ። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ በዚህ የቀውስ ጊዜ አንድም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ረጅ ድርጅቶች የዋግን ህዝብ ለመታደግ የሰሩት ስራ አለመኖሩን ስታይ ግራ ይገባሀል። አሁንም በእንዲህ ያለ ህይወት ውስጥ ሆኖ በዘላቂነት አካባቢው እና የዋግ ህዝብ መልሶ የማቋቋም ጉዳይስ ታስቧልን? አሁን ማንም የዋግ ተወላጅ እና የዋግ ደጋፊ የዋግ ህዝብ በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለ ታውቆ እንደ ሀገርም ሆነ በውጭ ሀገር ዋግ መልሶ እንዲቋቋም በየትኛውም አግባብ ካልተሰራ ዋግ አሁንም ብዙ እርምጃዎች ወደ ኋላ ያስቀረ ሁኔታ ላይ ወድቃለች። ቀጣይ አካባቢው ነጻ ሲሆን እንደ ብሄረሰብ አስተዳደር ዝርዝር መረጃዎችን ይዘን ምናቀርብ ሆኖ አሁናዊ ሁኔታው ግን ዋግ ከላይ ካስቀመጥነው በከፋ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ለዋግ ምድር እና ለዋጎች መልሶ መቋቋም የበኩልዎን ይወጡ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply