You are currently viewing “እንደ ሃገርስ ቢሆን ይሄን ቋሚ ገመና ተሸክመን የት ልንደርስ ነው?” አቶ የሱፍ ኢብራሂም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ …    ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ/ም           አዲስ አበባ ሸ…

“እንደ ሃገርስ ቢሆን ይሄን ቋሚ ገመና ተሸክመን የት ልንደርስ ነው?” አቶ የሱፍ ኢብራሂም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸ…

“እንደ ሃገርስ ቢሆን ይሄን ቋሚ ገመና ተሸክመን የት ልንደርስ ነው?” አቶ የሱፍ ኢብራሂም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ወለጋ ውስጥ በአማራዎች ላይ የሚፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሰውናል። በዚህ መሰረት በዛሬው እለት በኪረሙ ወረዳ በህፃናት እና እናቶች ላይ ሳይቀር መጠነ-ሰፊ፣ የተቀናጀ እና ዘግናኝ ጭፍጨፋ እየተካሄደ ነው። አስክሬኖችን ማንሳትና መቅበር እንኳን እንዳልተቻለ ታውቋል። ይሄ ለእኛ አሳዛኝ ብቻ አይደለም፤ አሳፋሪና አዋራጅም ነው! እንደ ሃገርስ ቢሆን ይሄን ቋሚ ገመና ተሸክመን የት ልንደርስ ነው? ከእንግዲህ ሌላውን ሁሉ ተውት—ከምር የህሌና እዳ ያለብን ወገኖች ትኩረት ሰጥተን መፍትሄ ብንፈልግለት ጥሩ ነው! በተጨማሪም ዘግየት ብሎ ባጋራው መልዕክቱ የሚከተለውን ብሏል:_ “በደቡብ አቅጣጫ የሚኖሩ አማራዎች ሕይወት ያን ያክል ዋጋ የለውም” የተባለ ይመስላል። ይሄ በፖለቲካችን ውስጥ የሕይወት ዋጋ የማንነት፣ የወገንነት እና የመብት ሳይሆን የፖለቲካ ፍጆታ ጉዳይ መሆኑን ያሳብቃል። – በሌላ በኩል “ራሳቸው በመንግስት ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ ማሳደር የማይችሉ ሃይሎች ንፁሀንን በመጨፍጨፍ ጫና ለመፍጠር ነው…” የሚሉ አካላትም እንዳሉ ይታወቃል። ለአመታት ሕፃናት እና እናቶች ሲጨፈጨፉና አስክሬናቸው የትም ሲጣል ከተጎዱት ሌላ የተጎዳ፣ በፖለቲካ እና በሕግ ተጠያቂ የተደረገ አካል ታይቶ ይታወቃል? እውነታው ይሄ አይደለም! የተቀናጀ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው!

Source: Link to the Post

Leave a Reply