እንደ ህዝብ የተከፈተብንን ጦርነት እኛም ወደ ጦር ግንባር በጋራ በመክተት እንመክተዋለን ሲሉ በምዕራብ ጎጃም ዞን የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ዘማቾች ተናገሩ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት…

እንደ ህዝብ የተከፈተብንን ጦርነት እኛም ወደ ጦር ግንባር በጋራ በመክተት እንመክተዋለን ሲሉ በምዕራብ ጎጃም ዞን የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ዘማቾች ተናገሩ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሃይል በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን ወረራ እና ጥቃት በተባበረ ክንድ ለመመከት እና ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት መንግስት የክተት አዋጅ ጠርቷል፡፡ በዚህም በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ታጣቂዎች እንዲሁም በዚህ ታሪካዊ የክተት ጥሪ ላይ መሳተፍ እንፈልጋለን ያሉ ህዝባዊ ሃይሎች ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡ በዚህ የክተት ጥሪ ላይ በመዝመት ሽኝት ሲደረግላት ያገኘናት ወጣት እማዋይ ሃይማኖት እንደምትለው አሁን ላይ በሃገራችን ህልውና ላይ ከባድ አደጋ ተጋርጧል ብላለች፡፡ በተጨማሪም በዚህ ሰዓት ሴቱም ወንዱም በጋራ በመውጣት የተከፈተብንን ወረራ እና ጥቃት መመከትም ያስፈልጋል፤ ሁሉም ሰው ወጦ ሀገሩን ማዳን ይኖርበታልም ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች፡፡ ሌላው ዘማች ደረጀ ፀሐይ በበኩሉ ወራሪው እስከዛሬ ድረስ የሃገሪቱን ሃብት እና ንድረት ሲዘርፍ ኖኗል፡፡አሁን ላይ ግን በክልላችን ላይ የከፈቱትን ጥቃት ለመመከት ሆ ብሎ በመነሳት የዘራፊውን ቡድን ግብዓተ መሬት መፈፀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ወጣቱም በግንባር ከመሳተፍ በተጨማሪ አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ መቻል አለበት የሚል መልዕክትን አስተላልፈዋል፡፡ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ሃላፊ ም/ኮማንደር ዋለልኝ አጥናፉ እንደሚሉት ደግሞ ሁሉም አካል በሙሉ ዝግጅት ላይ ነው የሚገኘው፤ ይህንን ወራሪ እና ዘራፊ ቡድን ለመደምሰስ ሁሉም አካል በንቃት መሳተፍ መቻል ይኖርበታል ብለዋል፡፡ የወረዳው የሰላምና የህዝብ ደህንነት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ታደለ ልመንህ ወራሪው ቡድን በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ሰው ለማድረግ ቀርቶ የማያስባቸውን አሰቃቂ ድርጊቶች እየፈፀመ ይገኛል ይላሉ፡፡ ሰቆቃው እና ዘረፋው ከዚህም በላይ ሳይባባስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ህዝቡን በማነቃነቅ ወደ ግንባር ጉዞ ጀምረናል ብለዋል፡፡ ይህንን ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥም በየትኛውም አካባቢ ያለ አካ ሁሉ ተሳታፊ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህ ዘመቻ ላይ የህክምና ባለሙያዎች እና አመራሮችም ግንባር ቀደም ተሰላፊ ሆነው አብረው ወደ ግንባር አምርተዋል የዘገበው የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply