እንዴት አደራችሁ!የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የማለዳ ዜናዎችን እንዲከታተሉ እንጋብዝዎታለን፡፡የተለያዩ አዳዲስ የሃገር ዉስጥና አለማቀፋዊ ዜናዎችን አዘጋጅተን እጠብቃችኋለን፡፡ከምትሰሟቸው ጉዳዮ…

እንዴት አደራችሁ!

የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የማለዳ ዜናዎችን እንዲከታተሉ እንጋብዝዎታለን፡፡

የተለያዩ አዳዲስ የሃገር ዉስጥና አለማቀፋዊ ዜናዎችን አዘጋጅተን እጠብቃችኋለን፡፡

ከምትሰሟቸው ጉዳዮች መካከል፡-

-በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ጃሌ ጥሙጋ ወረዳ እና በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት እና ኤፍራታና ግድም ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች በድጋሚ ግጭት ማገርሸቱ ተነግሯል፤ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ግጭቱ የጀመረው ቅዳሜ ለት ነው፤በዜናችን ትሰሙታላችሁ!

-የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት የሦስት አዳዲስ ሚንስትሮችን ሹመት አጽድቋል፤በመንግስት ውስጥ “በየጊዜው የሚካሄደው” የሚስትሮች ሹመት ግን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ ተነስቶበታል፤“ለምንድን ነው በየዓመቱ እንደ ዘመን መለወጫ ሚኒስትር የምንቀያይረው?” የሚል አስተያየትን አስተናግዷል፤ ዘርዘር አድርገን ይዘነዋል!

-በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ በዋግህመራ ልዩ ዞን ከ67 ሽህ በላይ ዜጎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸው ተነግሯል፡፡
በተለይም በህወሃት ቁጥጥር ስር በሚገኙት አበርገሌና ጸሃግብጂ ወረዳዎች ችግሩ እጅግ የከፋ ነው ተብሏል- ሰፋ አድርገን ፈትሸነዋል!

-በመንገዳችን ላይ ጥንቅራችን- በተሸከርካሪ የተለያዩ ወንጀሎች ሲፈጸሙ፣ እነዚህን ወንጀለኞች ለመያዝ የታርጋው ሁኔታ ለመያዝ ውስብስብ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡
የአሽከርካሪ- ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የታርጋ ቁጥር በአንድ ወጥ በሆነ መንገድ ለማስተካከል ማሰቡን እና ጥናት መጀመሩን ተገልፆ የነበረ ቢሆንም አሁንም ድረስ መፍትሄ አልተሰጠውም፤ታደምጡታላችሁ

-ለጤናችን፡- ዛሬ ስለ ጉሮሮ ቁስለት ምንነት፣መንስኤና ህክምናው ያስደምጣችኋል

-ኢትዮ ገበያ፡-ነጋዴው እና ሸማቹ ሲማረርበት የሰነበተው የሲሚንቶ ዋጋ ንረት እና የስሚንቶ ምርት መጥፋት አሁን የተወሰነ መረጋጋት እየታየበት መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ባደረገው ቅኝት ታዝቧል፡፡
የሲሚንቶ እጥረት እና የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር በተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች በሲሚንቶ ምርት እና ዋጋ ላይ ምን ውጤት አመጣ? ትሰሙታላችሁ!

-የዓለም ጉዳይ:- በአሜሪካ ባለፉት 50 አመታት በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ጥቃት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡
በሃገሪቱ በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ የሚፈጸም ግድያ ዛሬም ድረስ አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል፤ዓለምን አረጋጋለሁ በሚል የምትባዝነው ሃገር የራሷን ዜጎች መጠበቅ ስለምን ተሳናት? በትንታኔ አዘጋችተነዋል!

-ፖፕ ፍራንሲስ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊያቀኑ ነው፤አስቀድመውም አጃቢዎቻቸውን ልከዋል

-የዩክሬን ከፍተኛ አመራሮች የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤዎችን እያስገቡ ነው፤መሪያቸው ዘሌንስኪ ላይም የሰላ ትችት መሰንዘር ጀምረዋል

-አየርላንድ እስራኤልን በአለም አደባባይ እየተቸች ነው፤ለፍልስጤም ካሳ ትክፍል እያለችም ትገኛለች፤

ኢትዮ ማለዳችን እነዚህንና ሌሎችንም ጉዳዮች ይዟል፤በርናባስ በላይነህ የዛሬ ኢትዮ ማለዳ አስተናጋጃችሁ ነው፤
ማለዳችሁን ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ጋር እንድታደርጉ እንጋብዛችኋለን
ለአስተያየትና ጥቆማዎቻችሁ የአጭር የጽሁፍ መልክዕት መቀበያችንን 6321 ተጠቀሙ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply