#እንድታውቁት#ለአሽከርካሪዎችበአዲስ አበባ ከመንገድ ኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ ዝግ ሆነው የቆዩ የተወሰኑ መንገዶች ለተሸከርካሪዎች ክፍት ተደርገዋል፡፡ ሰሞኑን በኮሪደር ልማት ምክንያት ለተ…

#እንድታውቁት#ለአሽከርካሪዎች

በአዲስ አበባ ከመንገድ ኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ ዝግ ሆነው የቆዩ የተወሰኑ መንገዶች ለተሸከርካሪዎች ክፍት ተደርገዋል፡፡

ሰሞኑን በኮሪደር ልማት ምክንያት ለተሽከርካሪዎች ዝግ ከተደረጉ መንገዶች መካከል:-

1፤በቱሪስት ራስ መኮንን አድርጎ ወደ አፍንጮ በር እንዲሁም
2፤ከአፍንጮ በር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወደ ባሻ ወልዴ የሚወስደው መንገድ ለተሽከርካሪዎች ክፍት ተደርጓል።

በአካባቢው ላይ እየተከናወነ ባለው የልማት ስራ ምክንያት ለተሽከርካሪዎች ክፍት በተደረገው መንገድ ዳር ላይ፣ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭር ጊዜም ሆነ ለረዥም ግዜ ተሽከርካሪን ማቆም ፍጹም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ጽቤት አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply